ሲሪል ራማፎሳ በድጋሚ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ በአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ  እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የተደረገውን ጉልህ የሆነ የጥምር ስምምነት…

ሲሪል ራማፎሳ በድጋሚ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።

የደቡብ አፍሪካ ፓርላማ በአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ  እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል የተደረገውን ጉልህ የሆነ የጥምር ስምምነት ተከትሎ ሲሪል ራማፎሳን የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል።

አዲሱ የብሔራዊ አንድነት መንግሥት የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ፣ ዴሞክራቲክ አልያንስ፣ የአርበኞች ግንባር እና የኢንካታ ነፃነት ፓርቲን ያጣመረ መሆኑ ተገልጿል ።

ራማፎሳ በንግግራቸው ላይ  አዲሱን ጥምረት አድንቀው መራጮች ከመሪዎቻቸው   “በአገራችን ውስጥ ላለው ሁሉ መልካም ነገር  በጋራ እንዲሰሩ እንደሚቢጠብቁ  “ተናግረዋል፡፡  

የራማፎሳው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ በምርጫው ከፓርላማው መቀመጫዎች 40 % ድምፅ ብቻ በማግኘቱ በተናጠል መንግሥት ለመመሥረት ባለመቻሉ በምርጫው በ22% ድምፅ  ሁለተኛውን ከፍተኛ መቀመጫ ካገኘው ዴሞክራቲክ አሊያንስ ጋር ለመጣመር ከስምምነት ላይ ደርሷል።

ደቡብ አፍሪካውያንም ይህ ከዚህ በፊት ታይቶ የማያውቅ ታላቅ ጥምረት እንዲሳካ እንደሚፈልጉ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል።

በሐመረ ፍሬው

Source: Link to the Post

Leave a Reply