ሲኤንኤን በኮቪድ ሳቢያ ቢሮዎቹን በከፊል ዘጋ

የዜና ማሰራጫ አውታር ሲኤንኤን እየጨመረ በመጣው የኮቪድ-19 ቫይረሰ ሳቢያ መሰረታዊ አገልግሎት ከሚስጡ ሠራተኞቹ ውጭ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሚገኙ ሠራተኞቹ በሙሉ ቢሮዎቹ ዝግ መሆናቸውን ያስታወቀ መሆኑን ሮይተርስ ዘገበ፡፡

ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ለውስጥ ሠራተኞች ተላለፈ ያለውን የውስጥ ደብዳቤ ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው፣ የኤቲኤንቲ እና የዋርነር ሚዲያ አካል የሆነው ሲኤንኤን፣  ቢሮ ውስጥ የግድ መስራት ለሌላባቸው ሠራተኞቹ በሙሉ ወደ ቢሮዎቹ እንዳይመጡ መታዘዛቸውን አስታውቋል፡፡

ሲኤንኤን በስቱዲዮዎችና የስርጭት መቆጣጠሪያው ክፍል ውስጥ ያሉትን ሠራተኞች ቁጥር መቀነሱም በዘገባው ተመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply