“ሳሊን ፍለጋ”- የዚያ ትውልድ አሻራ ሲገለጥ – BBC News አማርኛ

“ሳሊን ፍለጋ”- የዚያ ትውልድ አሻራ ሲገለጥ – BBC News አማርኛ

https://ichef.bbci.co.uk/news/1024/branded_amharic/10594/production/_116546966_whatsappimage2020-12-18at15.50.39-2.jpg

‘አራት ሴቶች መስዋዕትነት በተከፈለባት በአሲምባ ኮረብታ ላይ ጮክ ብለው ይጣራሉ።”ሳሊ፣ ሳሊ፣ ሳሊ፤ ሰላማዊት” – ድምፃቸው በተራራው መካከል ይሰማል። የገደል ማሚቶው ድምፅም ሳሊ፣ ሰላማዊት እያለ በከፍተኛ ድምፅ ያስተጋባዋል። ተራራውም ስሟን መልሶ የሚጣራ ይመስላል። እነዚህ ሴቶች ማን ናቸው? ስሟን የሚጠሯትስ ሳሊ ወይም ሰላማዊትስ?በእድሜ ጠና ያሉት እነዚህ ሴቶች ክብረ፣ መንቢ፣ ብሩክታዊትና ፅዮን ናቸው። የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓን) የትጥቅ ትግል ተቀላቅላ ከአርባ አመት በፊት የጠፋችው እህታቸውን ሳሊ (ሰላማዊት ዳዊትን) ስም ነው የሚጠሩት።

Source: Link to the Post

Leave a Reply