ሳውዲ ዓረቢያ የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ በአደራዳሪነት መግባት እንደምትፈልግ የሱዳን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

የሳውዲ የአፍሪካ ጉዳዪች ተጠሪ አህመድ ቢን አብዱል አዚዝ ካታን እንዳሉት የሀገሪቱ ንጉስ ሳልማን ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና የግብፁ ፕሬዝዳንት አብድል ፋታህ አል-ሲሲ ጋር በግድቡ ዙሪያ እንዲመክሩ ጠይቀዋቸዋል፡፡ከሰሞኑ በሱዳን ጉብኝት ያደረጉት ተጠሪው፤ በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መካከል ያለውን አለመግባባት በድርድር ለመፍታት ሳውዲ ፍላጎት እንዳላት የሱዳን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ አመላክቷል፡፡

እንደ መግለጫውም ከሆነ፤ ሳውዲ የአረብ ሀገራት የውሃ አቅርቦት ዕጥረት እንዳያጋጥማቸው የምትችለውን ሁሉ ድጋፍ ታደርጋለች፤ ይህ ሲባል ግን የሦስቱን ሀገራት የተጠቃሚነት መብት በማያጥስ መልኩ መሆኑን ተጠሪው ተናግረዋል፡፡እንደ አናዶሉ ዘገባ ከሆነ የግድቡን ድርድር ከአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በተጨማሪ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች፣ የአወሮፓ ህብረትና አሜሪካ በታዛቢነት እየተከታተሉት ነው፡፡

አሐዱ ስለጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያ ለመጠየቅ ወደ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ያደረገው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡ ሚኒስቴሩ ባለፈው ማክሰኞ ሊሰጠው ያቀደውን ሳምንታዊ መግለጫም ሰርዞ ነበር፡፡ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስም ለመገናኛ ብዙሃን የሰጠው መግለጫ የለም፡፡

ቀን 12/06/2013

አሐዱ ራዲዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply