ሳዑዲ አረቢያ ለጋዛ ዕርዳታ የሚዉል ድጋፍ ማድረጓ ተገለጸ፡፡ሳዑዲ አረቢያ ለጋዛ ዕርዳታ የሚዉል ድጋፍ በአዉሮፕላን፣ በመርከብ እና በጭነት መኪና መላኳ ነዉ የተገለጸዉ፡፡አገሪቱ 36 አዉሮፕላ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/Y0hl0VwK2zdhNS55jREoUVeCTPXl_a553Cq3ipY-pGDseEiBtrApaqjYTMpJ0EPR7-KWTADedtYq_wXZsPiXgMdXDHClFe8f1A9q0gTaPa7iR7dOhw1pAe0Tl4T_VVhMgNGZZLZowRSTj4upnJA4FDwUrBwZ6lTSQD8BW6Tp6g6wNYfjY7QbVqEKxZgzoAjSZacZtDSHJv180i5bmian-HIzRD_ObdNlgdisOIMst-xP57pG5IdZlOHiaXZ8YsoXdYJNAgH9s5Rxhe1X97eOoHzcp1C0ukAzPw6qDMaGBjg7eUPHhNYj_u-CELiWBit7W8jQmSdO7dJgjfiSeBFRWg.jpg

ሳዑዲ አረቢያ ለጋዛ ዕርዳታ የሚዉል ድጋፍ ማድረጓ ተገለጸ፡፡

ሳዑዲ አረቢያ ለጋዛ ዕርዳታ የሚዉል ድጋፍ በአዉሮፕላን፣ በመርከብ እና በጭነት መኪና መላኳ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

አገሪቱ 36 አዉሮፕላኖችን፣ 5 መርከቦችን እና 1መቶ72 የጭነት መኪኖችን ነዉ ወደ ጋዛ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርሱ የላከችዉ፡፡

ከንጉስ ሰልማን የሰብዓዊ ዕርዳታ ማዕከል የተነሳዉ የአዉሮፕላን ድጋፍ 24 ቶን የምግብ እና የመድሃኒት ቁሳቁሶችን የያዘ ሲሆን፤ ከሪያድ ለራፋህ ድንበር ቅርብ ወደሆነዉ ወደ ምዕራብ ግብጽ መድረሱ ተገልጿል፡፡

ከሳዑዲ አረቢያ የተነሳዉ ሌላዉ የመርከብ ድጋፍ ደግሞ 4መቶ ቶን የምግብ እና የመጠለያ ቁሳቁሶችን ይዟል፡፡

በዉስጡም መጠለያ ድንኳን እና ብርድልብሶችን ከ3መቶ የኦክሲጅን ሲሊንደሮች ጋር የያዘ ነዉ፡፡

16 የሰብዓዊ ድጋፍ የያዙ የጭነት ተሸከርካሪዎችም ከሳዑዲ አረቢያ የተነሱ ሲሆን ፤ አገሪቱ እስከዛሬ የላከችዉን የዕርዳታ ጭነት መኪኖች ቁጥር 1መቶ 72 አድርሶታል ሲል ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

እስከዳር ግርማ

ጥር 08 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Telegram (https://t.me/ethiofm107dot8

Source: Link to the Post

Leave a Reply