ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሶስት ዓመት ዉስጥ 5ሺህ የቴሌኮም ማማዎች ለመገንባት ማቀዱን አስታወቀ።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከዉዳ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ 68 የካሞፋላጅ የቴሌኮም ማማዎችን ለመረከብ መስማማቱም ተገልፃል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለነዚህ ማማዎች ለዉዳ ብረታብረት 50 ሚሊዮን ብር መከፈሉን ጣብያችን ሰምቷል።

በስምምነቱ መሠረት እስካሁን 13 የቴሌኮም ማማዎችን ተረክቦ በመገጣጠም ላይ እንደሚገኝ ሁለቱ ድርጅቶች በሰጡት መግለጫ ገልፀዋል።

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዊም ቫንሄሌፑቴ “ይህ ወቅት ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ታሪካዊ ነዉ” ያሉት ሲሆን “የማማዎቹ ጥራት ጥሩ እና ወጪ ቆጣቢ ነዉ” ሲሉ ተደምጠዋል።

” እንደዚህ አይነት ስምምነቶች የሀገር ዉስጥ ኢንዱስትሪዎችን ለመደገፍ እና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩላችንን አስተዋፅእ የምናደእግበት ነዉ” ብለዋል።

“ይህ በኢትዮጵያ ማኑዩፋክቸሪንግ ትልቅ ምዕራፉ ነዉ” ያሉት ደግሞ የዉዳ ብረታብረት ዋና ስራ አስኪያጅ ስቴቨን ኪዩ ናቸዉ።

ስራ አስኪያጁ “ለሳፋሪኮም ማማዎችን በማቅረብ የመጀመሪያዉ ሀገር በቀል ተቋም በመሆናችን ኩራት ይሰማናል” ብለዋል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በሶስት ዓመት ዉስጥ በ1.5 ቢሊዮን ዶላር የኔትወርክ ማስፋፊያ በማድረግ 5000 የቴሌኮም ማማዎችን ለመገንባት አቅዷል።

ተቋሙ በአሁን ሰዓት ከ2,800 በላይ የቴሌኮም ማማዎች አሉት።

ዉዳ ብረታብረት ኢንዱስትሪ ከ18 ዓመታት በላይ ለቴሌኮሙኒኬሽን ፣ለብሮድካስቲንግ እና የቴሌቪዥን ሴክተሮች ማስተላለፊያ ማማዎች አምራች ድርጅት ነዉ።

ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም

በአቤል ደጀኔ

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply