ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ኔትዎርኩን በይፋ አስጀመረ

ሰኔ 04 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ሆኖ ከሶስት ዓመታት በፊት ስራ የጀመረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በጦርነት ሳቢያ ሳይደርስ የቆየውን የትግራይ ክልል በይፋ ተደራሽ ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል አማራጭ ጥራት ያለው ኔትዎርክ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ከጦርነት ጉዳት ለማገገም እና ለመልሶ ልማት አስተማማኝ አጋር እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል።

ጌታቸው ረዳ በክልሉ ከነበረው ጦርነት በኋላ የማህበራዊ አገልግሎቶች በድጋሜ ወደስራ መመለስ አካል በመሆኑ ትልቅ እርምጃ ነው ብለዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply