ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከ1 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች የ07 ኔትወርክን በመቀላቀላቸው እና ምርት እና አገልግሎቶችን በመጠቀማቸው ተሸላሚ የሚሆኑበትን የመጀመሪያ የደንበኞች የሽልማት መርሐ ግብርን ነው ዛሬ እለት ያስጀመረው፡፡
ለ14 ሳምንት ይቆያል የተባለው “ተረክ ጉርሻ” በተሰኘው የሽልማት መርሐ ግብር ደንበኞች የሳፋሪኮም ሲም ካርድ ሲያወጡ ፣ አየር ሰዓት ሲገዙ እና ጥቅሎችን ሲሞሉ እንዲሁም ጥቅሎችን ሲጠቀሙ ባለዕድለኞችን ብቁ የሚያደርግ የዕጣ ቁጥር መሆኑን ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።
➨የዕጣ መርሐ ግብሩ በየወሩ ለዕጣ የሚቀርቡ ሦስት መኪኖች፣
➨በየሁለት ሳምንቱ ሦስት ባጃጆችና ሰባት ሞተር ሳይክሎች፣
➨ስማርት ስልኮች፣ታብሌቶች እና የአየር ሰዓት ቦነሶች መኾናቸውን የሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዋር ሱሳ ገልጸዋል፡፡
እያንዳንዱ ደንበኛ በቀን ውስጥ 10 የእጣ ቁጥሮችን የሚያገኝ ሲሆን ቁጥሮቹም የዕለት ፣የሁለት ሳምንት እንዲሁ የወር ሽልማቶችን ለማሸነፍ በሚወጡ እጣዎች ውስጥ የሚካተቱ ይሆናል ተብሏል።
በዚህም መሰረት በእጣ አወጣጥ ስነስርዓቱ እድለኛ የሚሆኑ ደንበኞች በየወሩ ለእጣ የሚቀርቡ ሦስት መኪናዎችን ተሸላሚ ይሆናሉ ማለት ነው ።
በተጨማሪም በየሁለት ሳምንቱ ለእጣ የሚቀርቡ ሰባት ባጃጆች እና የሞተር ሳይክል እንዲሁም ስማርት ስልኮችን ፣ታብሌቶችን እና የአየር ሰዓት ይሸለማሉ ተብሏል።
ሲም ካርድ በመግዛት ኔትወርኩን ለሚቀላቀሉ አዳዲስ ደንበኞች በ24 ሰዓት ውስጥ አየር ሰዓት ከሞሉ 3 የዕጣ ቁጥሮችን እንደሚያገኙም ገልጸዋል፡፡
የዕጣ መርሐ ግብሩ እስከ ሰኔ 28/2015 ዓ.ም የሚቆይ እንደኾነ እና ከ1 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ባለ ዕድል እንደሚያደርግ ተነግሯል።
በእሌኒ ግዛቸው እና መሳይ ገ/መድህን
መጋቢት 27 ቀን 2015 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast
ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን
Source: Link to the Post