ሳፋሪኮም የሥራ እንቅስቃሴውን በተመለከተ ለመንግሥት ማብራሪያ ሰጠበኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመጀመር እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ሳፋሪኮም፣ የሥራ እንቅስቃሴውን አስመልክቶ ለከፍተኛ የመንግ…

https://cdn4.telesco.pe/file/HY8WB-4Hxh_gpfwrFUNJOPYHEuiioMjqgh0uCpjWvJ7qWY140-s0HLPTDom7lpF-bTiEKgP8p7yDwiQfOUZxK3poZzhFxZPoHrvWj8FDwOTOLZssdphej6CstNYPQrujRvZpmiziHfNfdDmdgOzZqvnjNGKzM076SN925C3SUuQgrB-_Tgcm-LKBirVDaNfHo0PKeyGqjoOiusxIULsp-dR8BcN6l3-9x6ma9OGuCEDhHlFLB9X-MPRE572b6OqmcrVMhzS3viKkqguW7K3fHFWy0nvrcVT9NLFdCBZQd4GLoUfU62SR_hLnVqFgGCbmuq9jsPs3njpRC2iltXZi4Q.jpg

ሳፋሪኮም የሥራ እንቅስቃሴውን በተመለከተ ለመንግሥት ማብራሪያ ሰጠ

በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመጀመር እንቅስቃሴ ላይ የሚገኘው ሳፋሪኮም፣ የሥራ እንቅስቃሴውን አስመልክቶ ለከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎች ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የገንዘብ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በዋና ሥራ አስፈጻሚው ፒተር ንዴግዋ የተማራው የሳፋሪኮም ልኡክ፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ሺዴ እና ሚኒስቴር ዲኤታው ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

በዚሁ በገንዘብ ሚኒስቴር ፍሬያማ በተባለው ውይይት ወቅት የሳፋሪኮም ኃላፊዎች ተቋማቸው በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየሠራ የሚገኘውን እንዲሁም ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል ነው የተባለው፡፡

ከመንግስት የሥራ ኃላፊዎቹ መካከል የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ መንግስት በቴሌኮሚኒኬሽን አገልግሎቶች ጥራት እና ስርጭት ጋር ተያይዞ ለሳፋሪኮም ድጋፍ እንደሚደርግም ገልጸዋል መግለጻቸው ተመላክቷል፡፡

ሳፋሪኮም የሚመራውና አምስት ኩባንያዎች እና ተቋማትን ያካተተው ‹‹ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ›› የተሰኘው ጥምረት የሚያቋቁመው ኩባንያ፤ በኢትዮጵያ የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት የማቅረብ ስራውን በጥር 2014 ለመጀመር እንዳቀደ ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

ሳፋሪኮም ፣ ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያ” የተሰኘው ጥምረት የኦፕሬሽን ፈቃድ የኦፕሬሽን ፈቃድ ለማግኘት 850 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ አቅርቦ ማሸነፉ ይታወቃል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሐሴ 26 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply