የከ’ሴራው ነፃ ነዎት ጥያቄ ጉዳይ….
እውን ከሴራ ነጻ ነዎት? (አቶ ጌትነት ይርሳው የቀድሞው የአማራ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ)
ሴራ ያልከኝ በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ ጋር በተያያዘ በእኔ ላይ ጥርጣሬ ስላለህ ነው፡፡ (ዶክተር አብይ አህመድ )
ነገሩ እንዲህ ነው የብልጽግና ፓርቲ አዳማ ላይ ጠርቶት የነበረው የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ሲጠናቀቅ የአዴፓ (የአማራ ብልጽግና ፓርቲ) የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትና የተወሰኑ የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ጋባዥነት በማግስቱ የሚመረቀው የአንድነት ፓርክን እንዲጎበኙ ተደረገ፡፡ በዛው ዕለት ማምሻውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋር በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በዝግ ለውይይት ተቀመጡ፡፡
በውይይቱ ሦስት የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ ወይንም አስተያየት ካላቸው እንዲያቀርቡ እድል ተሰጣቸው፡፡ አንደኛው አመራር ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ታላቅ ክብር እንዳላቸው ገልጸው “ሽህ አመት ይንገሱ” ብለው መረቋቸው
ሁለተኛው አስተያየት ሰጭ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚወዱትን ልብ አቅልጥ ሙገሳ ካቀረቡ በኃላ ከዛም አለፍ ብለው “በዚህ እርስዎ ባሉበት ግቢ አትክልተኛ ሆኜ ብቀር ደስ ይለኛል” አሉ እየሳቁ ፡፡ በዚህን ጊዜ ግማሾቹ ተሰብሳቢዎች ክፉኛ መሳቀቅ ሲታይባቸው ገሚሶቹ ደግሞ የአመራሩን ንግግር በሳቅ አጀቡት፡፡
ሦስተኛው ተናጋሪ አቶ ጌትነት ይርሳው ነበሩ፡፡ አቶ ጌትነት ንግግራቸውን ሲጀምሩ እኔ አስተያየት የለኝም በማለት ነበር፡፡ “የኔ አስተያየት አይደለም ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እኔም እንደ ሰው አንድ ነፍስ ነው ያለኝ እና አብሬዎት ለመታገል እንዲመቸኝ ግልጽ ያልሆኑልኝ 4 ጥያቄዎችን ለመጠየቅ ነው በማለት ሀሳባቸውን ሲገልጹ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ፈገግ ብለው “ቀጥል” በማለት ወጣቱን መሪ መስማት ጀመሩ፡፡
አቶ ጌትነትም ጥያቄያቸውን ቀጠሉ “የመጀመሪያው ጥያቄየ እውን አፈወ ላይ ያለችው ኢትዮጵያ ልበዎ ላይ አለች ወይ? ከጀርባዎ ምንም አይነት ሴራ የለም ወይ? አሏቸው፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩም በቅጽበት ፊታቸው ተቀያየረ፡፡ በእጅጉ ተናደዱ፡፡ ብዙዎቹ የውይይቱ ተሳታፊዎች ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገቡ፡፡
አማራው አቶ ጌትነት ይርሳው ቁጭት በሚነበብበት ስሜት ውስጥ ሆነው ንግግራቸውን ቀጠሉ ፡፡ “ክቡርነትዎ ይህንን የምጠይቀዎት እውነታውን ከእርስዎ አረጋግጨ አብሬዎት ለመታገል ስለፈለኩ ነው፡፡ አሁን ምኑም ሳይገባቸው በደፈናው የሚያመሰግኑዎት አድር ባዮች ሁሉ ኃላ ላይ ከእርስዎ ጎን አይገኙም፡፡ እውነታን ይዘን ከተግባባን ግን ለዚህች ሀገር እና ለሰፊው ህዝብ ብለን አብረን መስዋዕት መሆን እንችላለን፡፡ ይህንን ጥያቄ በማንሳቴ ቅር እንዳይሰኙብኝ ባሳለፍኩት 33 የልጅነት እና የወጣትነት ዕድሜየ ያየሁት አንድ እውነታ ቢኖር ያለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ ፖለቲካ የሴራ ፖለቲካ በመሆኑ በየጊዜው የሚመጡት መሪዎች (ማለቴ መሪዎች ሳይሆኑ ነጅዎች) እና መዥገሮች በመሆናቸው የአማራውን ህዝብም የዚህ የሴራ ፖለቲካ ሰለባ በማድረጋቸው እና አሁን በብልጽግና ፓርቲ ላይም የማያቸው ነገሮች ከፍተኛ የተረኝነት እና በርካታ ነገሮች ጥርጣሬ ውስጥ ስለከተቱኝ ጀርባዎ ምን ያህል ከሴራ ነጻ ስለመሆኑ በአንደበተዎ እንዲያረጋግጡልኝ ስለፈለኩ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ስለሌሎች የማያገባኝ ሲሆን በግሌ አብሬዎት ለመታገል አልችልም፡፡ በማለት አከታትለው 3 ገራሚ ጥያቄዎችን ጠየቋቸው፡፡
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግን እውነተኛው የአማራ ልጅ ቆራጡ ጌትነት ይርሳው ያቀረቡላቸውን የመጀመሪያውን ጥያቄ ሲመልሱ “ሴራ ያልከኝ በአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ግድያ ጋር በተያያዘ እጅህ አለበት ብለህ ስለምታስብ እንደሆነ ገብቶኛል፡፡ ለመሆኑ አንተ የየት አካባቢ ሰው ነህ? በማለት እስከመጠየቅ ደርሰው እንደነበር እና ለ2 ተከታታይ ስዓታት ከጉዳዩ ጋር ተያያዥነት የሌላቸው የግል ምልከታቸውን (ሃሳባቸውን) በመስጠት ስብሰባው መቋጨቱን ታማኝ ምንጮቻችን አረጋግጠውልናል፡፡
ከዛች ቀን ጀምሮ አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሚያ ፕሬዝደንት ሰሞኑን እውነታውን እንደነገሩን ታማኝ የሆኑ የአዴፓ ውስን አመራሮች ጌታችን ተናገርክ በሚል ከአቶ ጌትነት ይርሳው ጋር ሆድና ጀርባ ሆኑ፡፡ በጊዜ ሂደትም አቶ ጌትነት ከፍኖ ጋር በተያያዘና በሌሎች ተደራራቢ ሴራዎች ተጠናክረው ሲቀጥሉ እንዲሁም ከያዙት ሃቅ እና ከህዝቡ ውጭ የመሪዎች ድጋፍ የሌላቸው እንደሆነ ሲረዱ ውስጥ ሆኖ አላስፈላጊ መስዋዕትነት ከመክፈል ባለፈ ውስጥ ሆኖ ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል በመገንዘባቸው መልቀቂያ አስገብተው ከአመራርነት እንዲወጡ ተደረገ፡፡
ነጩዋ እውነት ይህች ናትና አዴፓ እውነተኛውን የህዝብ ልጅ ከቦታው እንዲለቅ ቀን ከሌት ግፊቶች በርክተው እንዲለቅ ሆኗል። ብአዴን የሚቆጭ ድርጅት ባይሆንም ከውስጥ ሆነው ለህዝብ የሚሰሩትን ግን እንዴት እንደሚገፉ ይህ ትልቅ ምስክር ነው።
https://www.facebook.com/search/top?q=%E1%8C%8C%E1%89%B5%E1%8A%90%E1%89%B5%20%E1%8B%AD%E1%88%AD%E1%88%B3%E1%8B%8D%20