ሴቭ ዘ ችልድረን ኢትዮጵያ ባለፉት 6 ዓመታት 8.3 ሚሊዮን ህፃናት የስነ ምግብ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉተነገረ:: ከስድስት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ 38 በ…

ሴቭ ዘ ችልድረን ኢትዮጵያ ባለፉት 6 ዓመታት 8.3 ሚሊዮን ህፃናት የስነ ምግብ ፕሮግራም ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉተነገረ::

ከስድስት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ከ5 ዓመት በታች የሆኑ 38 በመቶ ህፃናት ለመቀንጨር ችግር ተጋላጭ እንደነበሩ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።
ግብረ ሰናይ ድርጅቱ ይህንኑ የመቀንጨር ችግርን ለመቅረፍ የሚያስችል ስራ መስራቱን አስታዉቋል፡፡
በስድስት ዓመታት ጉዞዉ 8.3 ሚሊዮን ከአምስት ዓመት በታች ህፃናት የስነ ምግብ ፕሮግራም ተጠቃሚ ተደርገዋል ተብሏል።

ዛሬም በኢትዮጲያ የሚስተዋለው የስርዓተ ምግብ ችግር በእናቶች እና ህፃናት ላይ ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ይገኛል ሲሉ በሴቭ ዘ ችልድረን ኢትዮጲያ የስርዓተ ምግብ ፕሮጀክት ዋና ዳይሬክተር አቶ ልዑል ሀይሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ከስርዓተ ምግብ አለመስተካከል ጋር ተያይዞ በሚፈጠሩ ክፍተቶች ሳቢያ በኢትዮጵያ 38 በመቶ ህፃናት ለመቀንጨር ችግር ተጋላጭ እንደሚሆኑ ተነግሯል፡፡
ይህ አሃዛዊ መረጃ እንደሚያመላክተው ከአምስት ህፃናት ሁለቱ ለመቀንጨር ችግር ተጋላጭ ነበሩ ተብሏል።
ይህንኑ ችግር መቅረፍን ዋነኛ አላማ ባደረገው የዕድገት ስርዓተ ምግብ እንቅስቃሴ ሳቢያ ባለፉት ስድስት ዓመታት በኦሮሚያ ፤ አማራ ፤ ሲዳማ ፤ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በተሰራው ስራ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ 8.3 ሚሊዮን ህፃናት የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ተደርገዋል ሲሉ ሃላፊው አብራርተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ሴቭ ዘ ችልድረን ኢትዮጵያ ከስድስት ዓለም ዓቀፍ እና አምስት የሀገር ውስጥ አጋሮች ጋር በመተባበር መስራቱንም ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

በረድኤት ገበየሁ
ሐምሌ 22 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply