“ሴት ደፋሪ እና ገዳይ ቡድንን ለማንበርከክ እኛ ጀግና ሴት ፋኖዎች ወደ ጥምር ጦሩ ተቀላቅለናል” ሲሉ በወሎ ፋኖ አደረጃጀት የላስታ ላሊበላ ፋኖ ክንፍ ተመራቂዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕ…

“ሴት ደፋሪ እና ገዳይ ቡድንን ለማንበርከክ እኛ ጀግና ሴት ፋኖዎች ወደ ጥምር ጦሩ ተቀላቅለናል” ሲሉ በወሎ ፋኖ አደረጃጀት የላስታ ላሊበላ ፋኖ ክንፍ ተመራቂዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 7 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ሃይል በአማራና አፋር ክልል ሴቶችን በቡድን አስገድዶ ደፍሯል፤ በርካታ ሴቶችን ገሏል፤ በርካታ ሴቶች በህክምና እጥረት እንዲሞቱ አድርጓል፤ በርካታዎቹንም ከትውልድ ቦታቸውና ንብረታቸው አፈናቅሏል። ይህ ግፍ ያሰቃያቸው የሰሜን ወሎ ወጣት ሴቶች ወደ ፋኖ አደረጃጀት በመግባትና በመሰልጠን ወደ ጥምር ቡድኑ እየተቀላቀሉ ይገኛሉ። የእናት ሃገር ጥሪን ተቀብለው ወደ ጥምር ጦሩ የተቀላቀሉ ሴት ወጣቶች ሴት ደፋሪና ገዳይ ቡድንን ለማንበርከክ እኛ ጀግና ሴት ፋኖዎች ወደ ጥምር ጦሩ ተቀላቅለን አሸባሪውን ቡድን ለማንበርከክ ቆርጠን ተነስተናል ብለዋል ሲል መቄት ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply