You are currently viewing ሴቶች በማምረቱ ዘርፍ ላይ ያላቸው ተሳትፎ አናሳ ነዉ ተባለ፡፡

ሴቶች በማምረቱ ዘርፍ ላይ ያላቸው ተሳትፎ አናሳ ነዉ ተባለ፡፡

ይህ የተገለፀው የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ባዘጋጀው የሴቶችን ተሳትፎ በማምረቻው ዘርፍ ማረጋገጥ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ውይይት ነው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀና አርያስላሴ እንዳነሱት የሴቶች ተሳትፎ በግሉ ዘርፍ ብዙ እንዳለሆነ በመጎለፅ ተሳትፎውን መጨመር እና ማረጋገጥ እንደሚገባ ተነስቷል።

አካታች የሆነ የፋይናንስ ዘርፍ አለመኖርም ሴቶች በማምረቱ ዘርፍ በስፋት እንዳይገኙ እክል እንደሆነ ተነስቷል።

በተለይም የሴቶችን ተሳትፎ በማምረቱ ዘርፍ ማረጋገጥ ሀገሪቷ ለምታደርገው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወሳኝ እንደሆነ ያነሱት ሀላፊዋ መሬት ላይ ያለው ተሳትፎ ግን ገና እና ሊበረታታ እንደሚገባ ተነስቷል።

የአዲስ ቻምበር የምክር ቤት ሀላፊ ወሮ መሰንበት ሸንቁጤ በበኩላቸው፤ ሴቶች በየትኛውም መስክ ተፅዕኖ ፈጣሪ እንደሆኑ በማንሳት በንግዱ ዘርፍም ይህ ሊደገም እንደሚገባም አንስተዋል።

አሁን ላይ መንግስታዊ በሆኑ የቢዝነስ ዘርፍ ላይ የሴቶች እንቅስቃሴ ጥሩ እንደሆነ ሲገለፅ በግሉ ዘርፍ ያለው የሴቶች እንቅስቃሴ ግን ገና ሊበረታታ እንደሚገባ ተገስቷል።

በተለይም ሴቶችን ሊያበረታታ እና ተሳትፏቸውን ሊጨምር የሚችል የፋይናንስ አቅም በማምረቱ ዘርፍ ለሴቱ አምራች ሊሰጠው እንደሚገባ ተጠቁሟል።

በለአለም አሰፋ

መጋቢት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply