ስለሀገር እና ስለወገኑ በመታገሉ በካድሪዎች በመሳደድ ላይ የሚገኘው የፋኖ ማስተር ብርሃኑ ታላቅ ወንድም በቁጥጥር ስር ዋለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም…

ስለሀገር እና ስለወገኑ በመታገሉ በካድሪዎች በመሳደድ ላይ የሚገኘው የፋኖ ማስተር ብርሃኑ ታላቅ ወንድም በቁጥጥር ስር ዋለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሕልውና ዘመቻውን ተከትሎ በማይጠብሪ እና በላሊበላ ግንባር ተሰልፎ ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረገው የላይጋይንት ጀግና ዘውዱ ተፈራ በቁጥጥር ስር ውሏል። ዘውዱ ተፈራ ከሕልውና ዘመቻ ማግስት ጀምሮ በደካማ ካድሪዎች እየተሳደደ የሚገኘው የፕሮፌሽናል ቴኳንዶ አሰልጣኙ የፋኖ ማስተር ብርሃኑ ታላቅ ወንድም ነው። ግንቦት 18/2014 ከቀኑ 8:30 አካባቢ በላይጋይንት ወረዳ ታች ነገላ ቀበሌ 23 ከስራ ቦታው በመያዝ እንደ ህመምተኛ በአምቡላንስ ጭነው ወደ ነፋስ መውጫ ወስደውታል ተብሏል። የ23 ቀበሌ ሊቀመንበር በመሆን ለበርካታ ዓመታት ያገለገለ እና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ ተገልጧል። ሽባባው ደርብ የተባለ ሚሊሻ ወንድሙን በማይጠብሪ ግንባር የተነጠቀው ዘውዱ ተፈራ በትግሉ ላይ ትልቁን ሚና የተወጣ ነው። የፕሮፌሽናል ቴኳንዶ አሰልጣኙና በርካታ ፋኖዎችን በማሰልጠንና በማብቃት የሚታወቀው ፋኖ ማስተር ብርሃኑ ከዘመቻ ህልውና ማግስት ጀምሮ በወረዳው ውስጥ ባሉ ደካማ ካድሪዎች እየተሳደደ እንደሚገኝ ይታወቃል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply