You are currently viewing ስለሀገር እና ስለወገን ሲባል ከአሸባሪው ትሕነግ ጋር በተደረገው ተጋድሎ የተሰዋውን አስር አለቃ ኤፍሬም አጥናፉን ሻማ በማብራት ለመዘከር እየተንቀሳቀሱ የነበሩ የቀጠናው አስተባባሪን ጨምሮ 4…

ስለሀገር እና ስለወገን ሲባል ከአሸባሪው ትሕነግ ጋር በተደረገው ተጋድሎ የተሰዋውን አስር አለቃ ኤፍሬም አጥናፉን ሻማ በማብራት ለመዘከር እየተንቀሳቀሱ የነበሩ የቀጠናው አስተባባሪን ጨምሮ 4…

ስለሀገር እና ስለወገን ሲባል ከአሸባሪው ትሕነግ ጋር በተደረገው ተጋድሎ የተሰዋውን አስር አለቃ ኤፍሬም አጥናፉን ሻማ በማብራት ለመዘከር እየተንቀሳቀሱ የነበሩ የቀጠናው አስተባባሪን ጨምሮ 4 የፋኖ አባላት በአዲስ ቅዳም ታሰሩ። ባህርዳር :-የካቲት 24 ቀን 2014 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አመራር እና አባላትን ማሰሩ እና ማሳደዱ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ መሆኑ ተገልጧል። የካቲት 23/2014 በአዊ ዞን አዲስ ቅዳም የቀጠናው አስተባባሪን ጨምሮ ሌሎች ሶስት የአዲስ ቅዳም ፋኖዎች ታስረዋል። “ሳታስፈቅዱ ሻማ አበራችሁ፤ ዘከራችሁ” በሚል በቁጥጥር ስር ስለመዋላቸው ተገልጧል። የመራዊ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደጀን ቀጠና የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) ሰብሳቢ ፋኖ እስቲበል አለሙም በአዲስ ቅዳም ተገኝተው የሻማ ማብራቱን ለመካፈል እና ለማስተባበር ያደረጉት ሙከራ በእስሩ ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል። ከሳምንት በፊት የአማራ ህዝባዊ ኃይል ፋኖ አሰልጣኝ አዲሱ ቢተውን ለማፈንና ትጥቅ ለማስፈታት የተደረገውን ዘመቻ ህግ የማስከበር ሳይሆን የማፈን ተግባር ነው ሲሉ ያወገዙት ፋኖ እስቲበል አለሙ ከየካቲት 23 ቀን 2014 ጀምሮ ከሶስት የአዱስ ቅዳም የፋኖ አስተባባሪዎች ጋር ታስረው ይገኛሉ። በአዲሥ ቅዳም ገብርኤል ቤተክርሥትያን ተገኝተው በሻማ ማብራት ስለአማራ እና ስለሀገር የተሰዋውን አስር አለቃ ኤፍሬም አጥናፉን ለማሰብ እየተንቀሳቀሱ ሳለ የታሰሩትም:_ 1) እስቲበል አለሙ፣ 2) ተሻገር አደመ፣ 3) አንሙት ጌታሁን እና 4) ሀብታሙ ዘሪሁን የተባሉ የህዝባዊ ኃይሉ አመራር እና አባላት ናቸው። የካቲት 13/2014 ጨለማን ተገን በማድረግ በቁጥጥር ስር ለማዋል እንጅባራ ላይ ድንገተኛ ከበባ የተደረገበትና ለ11 ዓመታት በመከላከያ ውስጥ ያገለገለው የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አሰልጣኝ አዲሱ ቢተው “ገና ጁንታ መጥቶ ይመራኛል” የሚል አስተሳሰብ ያለው አመራር አለ፤ “የዓመት በዓል በግ ይመስል እጄን እና እግሬን ታስሬ ሳትንፈራገጥ ታረድ የሚል መልዕክት ነው እነሱ እየሰጡን ያለ፤ እኔ ደግሞ ተንፈራግጨ ነው የምሞት እያልኩ ነው።” ሲል መናገሩ ይታወሳል። ከአፈናው ጋር በተያያዘ “ያለ ጥፋቴ እጅ አልሰጥም፤ ትጥቅም አልፈታም” በሚል ጫካ የገባው የአሰልጣኝ አዲሱ ቢተው ጉዳይም እስካሁን መፍትሄ አለማግኘቱን ለማወቅ ተችሏል። የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አመራር እና የህግ ባለሙያው አስረስ ማረ ዳምጤ የካቲት 06 ቀን 2014 ዓ.ም በማቻክል ወረዳ አማኑኤል ከተማ በነበረው የፋኖ ምረቃ ስነ-ሥርዓት ላይ በተገኙበት ወቅት ፋኖ አሰልጥኖ፣ አደራጅቶ እና መርቶ ለወገኑ የተሰዋዉን የፋኖ አስር አለቃ ኤፍሬም አጥናፉ ምስል ያለበት ማስታወሻ ሲበረከትላቸው “ከባድ አደራ መሆኑን አውቃለሁ! አደራችሁን እንዳልበላ ፈጣሪ ይርዳኝ።” ማለታቸው ይታወሳል። አሚማ ያነጋገራቸው የአዲስ ቅዳም የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ኮሎኔል የትዋለ በለጠ ከአካባቢው አለመኖራቸውን በመግለጽ በቀጣይ አጣርተው እንደሚገልጹ ከመናገር ውጭ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ አስተያየት አልሰጡም። በአንጻሩ “በሻማ ማብራታቸው አላሰርንም” ሲሉ ያስተባበሉት የአዲስ ቅዳም ከንቲባ አቶ አዲሱ ፈጠነ መዘከር መብት ነው፤ የተሰዋውን ኤፍሬም አጥናፉንም እንደ ከተማ አስተዳደርም ሆነ እንደ ዞን ቀድመን እውቅና ሰጥተናል ብለዋል። በወንጀል ተጠርጥረው በፖሊስ የታሰሩ ሶስት ግለሰቦች መኖራቸውን በመግለጽ በፖሊስ ተጣርቶ ሪፖርት ሲደርስ የምንገልጽ ይሆናል ሲሉም አክለዋል። “አሁን ችግር እየሆነ ያለው ሰው ጥፋት ሲያጠፋ እና በህግ ሊጠየቅ ሲል ከፋኖ ጋር የሚያያዘው ነገር ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 Facebook :- https://www.facebook.com/asharamedia24 youtube :- https://www.youtube.com/channel/UChir2nIy58hlLQRYyHIQeHA

Source: Link to the Post

Leave a Reply