You are currently viewing ስለወቅታዊ ሁኔታ ከአማራ ፋኖ በወሎ የተሰጠ የአቋም መግለጫ =================================================== ሀገራችን ኢትዮጵያ በተከፈተባት የውስጥና የውጭ…

ስለወቅታዊ ሁኔታ ከአማራ ፋኖ በወሎ የተሰጠ የአቋም መግለጫ =================================================== ሀገራችን ኢትዮጵያ በተከፈተባት የውስጥና የውጭ…

ስለወቅታዊ ሁኔታ ከአማራ ፋኖ በወሎ የተሰጠ የአቋም መግለጫ =================================================== ሀገራችን ኢትዮጵያ በተከፈተባት የውስጥና የውጭ ጦርነት እንደ ሀገር ፈታኝ ወቅት ላይ እናገኛለን ።ይህንን የሀገራችንና የህዝባችን ፈታኝ የሆነበትን አስከፊ ዘመን እንደ አባቶቻችን በጥበብ መሻገር ካልቻልን የታሪክ ስህተት እንዳንሰራ እንፈራለን ። ኢትዮጵያን ለማፍረስ የአውሮፓና የምእራባውያንን ተልእኮ በመሸከም ሀገራችን እንድትፈርስ እየሰሩ ያሉ ልጆቸ ብላ ያሳደገቻቸው በውስጥ ጡት ነካሽ ባንዳዎች አማካኝነት ነው። የትግራይ ወራሪ ቡድን የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ከከፈተበት ወቅት ጀምሮ የውስጥ ባንዶች በመሰባሰብ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲኦል መግባት ካለብን ሲኦል ድረስ እንገባለን በማለት አቅማቸውን አሟጠው የነጮችን ሀ…ገር አፍራሽ ሴራ አንግበው እናት ሀገር ኢትዮጵያን ለዘርፈ ብዙ ችግሮች ዳርገዋታል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት ሲፈፅም የፌዴራል መንግስት የድረሱልኝ ጥሪ ባቀረበው መሠረት የአማራ ህዝብ ሀገርን ለማፍረስ የመጣውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ወደ መሀል ሀገር ዘልቆ እንዳይገባ በየግንባሩ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመሰለፍ የአንበሳውን ድርሻ ሲወጣ መቆየቱ ታሪክ የማይዘነጋው ሀቅ ነው። የትግራይ አሸባሪ ቡድን መሪ ነኝ የሚለው አፈቀላጤው ጌታቸው ረዳ እንደ ህዝብ የአማራን ህዝብ ለይቶ ሂሳብ እናወራርዳለን በማለት የትግራይ አሸባሪ ቡድን ወደ አማራ ክልል ዘልቆ ሊገባ የቻለው በዋናነት በፌዴራል መንግስት ቸልተኝነት ምክንያት ህዝባችን ለግማሽ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያን ሲዘርፍ የኖረ ወንበደ ቡድን ተሸክሞ በህዝባችን ላይ ኢሰብአዊ ድርጊቶች ሲፈፅም መቆየቱ ይታወቃል። የሚገርመው አሁንም የሰቆቃው ቆይታ እንደቀጠለ መሆኑ የበለጠ ችግሩን አንገብጋቢና አሰከፊ አድርጎት ይገኛል። የአማራ ህዝብ ሂሳብ ይወራረድበታል ተብሎ በተናገረው መሰረት ሀገሩን እንደ ሀገር ለማቆም ህዝብን ለመጠበቅ የአማራ ህዝብ ትጥቁን ታጥቆ ስንቁን ሰንቆ ጠላትን ፊት ለፊት በመፋለም ሀገሩን ከመፍረስ ህዝቡን ከእልቂት ለመታደግ ችሏል።የፌዴራልና የአማራ ክልል መንግስት ትጥቅ ያለው ትጥቅህን ይዘህ ትጥቅ የሌለህ ያለህን የጦር መሳሪያ በመያዝ ሀገርህንና ህዝብን ታደግ እንድሁም ግንባር ላይ ከጠላት የማረከውን የጦር መሳሪያ የግልህ ሁኖ ይመዘገብልሀል በማለት ለቀረበለት ለሀገር አድን ጥሪ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆነው ፋኖ ማቄን ጨርቄን ሳይል ያለውን በመያዝ በየግንባሩ በመገኘት ታላላቅ ጀብዶችን በመፈፀም ጠላትን መውጫ መግቢያ በማሳጣት ገድል ሲፈፅም ቆይቷል። በመሆኑ በየግንባሩ ለሀገራቸው ክብርና ለህዝባቸው መኖር ሲሉ ውድ ህይወታቸውን የሰጡ የአማራ ፋኖ ጀግኖች ለዘላለም በታሪክ መዝገብ ላይ ሲታወሱ ይኖራሉ።እንዲሁም ፋኖ ከጠላት ከነፍስ ወከፍ መሳሪያ እስከ ከፍተኛ የቡድን መሳሪያ በመማረክ ጠላትን መልሶ በመውጋት የባዳውን ሴራ አክሽፏል።የአማራ ህዝብ በአሁኑ ወቅት የገጠመው ጠላት ብሎ ከፈረጀው ጦርነት ከከፈተበት የትግራይ ወራሪ ሀይል በተጨማሪ ሌሎች አማራ ጠል ቡድኖች ጋር በመተባበር በቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ ክልል የአማራን ህዝብ በአማራነቱ ብቻ በጅምላ ተረሽነዋል ። በጅምላ በቤት ውስጥ ከነነፍሳቸው ተቃጥለዋል፤ ለዘመናት ጥረው ግረው ያፈሩት ንብረታቸው ተዘርፏል፣ ተቃጥሏል። ከሞትም የተረፉት በስደት ላይ ይገኛሉ ። ለአማራ ህዝብ መጨፍጨፍና መፈናቀል እንደ ሀገር ሀላፊነት በመውሰድ የህዝብን ሰላም ማስከበር የመንግስት ተቀዳሚው ስራ ሆኖ ሳለ ይህ ባለመፈፀሙ ምክንያት በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የአማራ ህዝብ ዋጋ እየከፈለ ይገኛል።የትግራይ አሸባሪ ቡድን ደቡብና ሰሜን ወሎ ለቆ ራያና ሰቆጣ የአማራን ህዝብ ርስት እንደያዘ ይገኛል። በትግራይ ክልል ህዝቡን በማሰልጠን ለዳግም ጦርነት ዝግጅት ላይ መሆኑ ይታወቃል።ይህንን መሰረት በማደረግና ህዝባችንን ከዳግም ወረራ ለመታደግ የሚከተሉትን ባለ ዘጠኝ ነጦቦች ያሉት የአቋም መግለጫ አውጥተናል። 1.በአማራ ክልል የትግራይ ወራሪ ሀይል በቆየባቸው አካባቢዎች የወደሙ መሰረተ ልማቶችን በአስቸኳይ እድጠገኑ 2.የትግራይ ወራሪ ቡድን የወሎ ራያና ሰቆጣ የአማራን መሬት ለቆ እንድወጣ የፌደራል መንግስት አስቸኳይ እርምጃ እድወስድ 3.በኦሮሚያ ክልል በማንነታቸው ምክንያት በኦነግ ሰራዊት ስለሚገደለውና ስለሚፈናቀለው የአማራ ህዝብ የፌደራል መንግስት የማያዳግም አስቸኳይ መፍትሔ እድወስድ 4.ከኦሮሚያ ክልል ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሜዳ ላይ ለወደቁ ተፈናቃዮች የክልሉና የፌደራል መንግስት አስቸኳይ ድጋፍ እዳደርግ 5.የትግራይ ህዝብ ከትግራይ ክልል በመፈናቀል ወደ አማራ ክልል እየገባ ያለው ህዝብ ህዝባችንን ለዳግም ወረራ ለመዳረግ ሌላኛው ስልት በመሆኑ ህዝባችን ከወትሮው በበለጠ አካባቢውን ነቅቶ እድጠብቅና መንግስት አስቸኳይ እርምጃ እድወስድ 6.የትግራይ ወራሪ ሀይል ከወትሮው በላቀ ህዝባችን ለመጨፍጨፍና ንብረቱን ለመዝረፍ ዝግጅት እያደረገ ባለበት ወቅት በአማራ ክልል ፋኖን አታሰልጥኑ በማለት በየአካባቢው የሚታሰሩና በፋኖ ላይ ተኩስ በመክፈት ህዝባችን ላይ ሌላ ችግር ለመፍጠር የሚሰሩ በየደረጃው ያሉ የክልሉ የመንግስት አመራሮች እየሄዱበት ያለው መንገድ አግባብነት ስለለው ከድርጊታቸው እድቆጠቡና መንግስት አካሄዱን እድያስተካክል 7.በአንዳንድ የአማራ ክልል አካባቢ የፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት መንግስት በሚያሰማራቸው የፀጥታ ሀይሎች ከፋኖ ሆደ ሰፊነት የተነሳ ወገን ላይ አልተኩስም በማለታቸው በመንግስት ትዕዛዝ በተሰጣቸው ሀይሎች በግፍ ለተገደሉ የአማራ ፋኖ አባላት መንግስት ይቅርታ እድጠይቅና ለቤተሰቦቻቸው ካሳ እድከፍል 8.የፌደራልና የአማራ ክልል የፀጥታ ሀይሎች አብሯችሁ ከጎናችሁ በመሆን ለአንድ አላማ የተዋደቀላችሁና ደጀን የሆናችሁን የአማራ ፋኖን ሀገርን ከመፍረስ ህዝብን ከመታረድ ያዳነ መሆኑን አውቃችሁ ከፋኖ አባላት ጋር ያለውን የግንኙነት አካሄድ መንግስት እንድያስተካክል 9.የአማራ ፋኖ ከጠላት የቀማውን የጦር መሳሪያ እንቀማለን ትጥቅ ያውርድ በማለት በየአካባቢው ግጭት እየፈጠሩ ያሉ የመንግስት የፀጥታ ሀይሎችን መንግስት ከድርጊታቸው እድቆጠቡ አስቸኳይ እርምጃ እድወስድ ስንል እንጠይቃለን። ከላይ የተቀመጡትን የአቋም መግለጫ ነጦቦች መንግስት በአስቸኳይ መፍትሔ የማይሰጥባቸው ከሆነ ህዝባችንን ከሞትና ከስደት ለመታደግ ሌሎች አማራጮችን የምነጠቀም መሆኑን እንገልፃለን።ህዝባችንም ለህዝባዊ ትግል ጥሪ እንደምናደርግ አውቃችሁ በተጠንቀቅ ትጠብቁን ዘንድ ጥሪያችንን እንስተላልፋለን!!!! አርበኝነት የማንነታችን አርማ ነው!!! አንድ አማራ ወሎ ደሴ መጋቢት 6/2014ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply