ስለ ቆረቆር በሽታ ምንነት ያውቃሉ ?

እንግዲያውስ ጣቢያችን በዚህ ጉዳይ ላይ ለእናተ ግንዛቤን ለመፍጠር ከሚመለከታቸው ባለሙያ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ባለሙያው ዶ/ር ዳዊት ዮሀንስ ሲሆኑ በጥላ የቆዳና የአባላዘር ልዩ ክሊኒክ የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት ናቸው።

ዶክተር ዳዊት ዮሐንስ ስለ ቆረቆር ወይንም የራስ ቅል ፀጉር እና የቆዳ ፈንገስ ምንነትን ሲገልፁ:-

ቆረቆር :-በፋንገስ የሚመጣ በብዛት የህፃናትን የራስ ቅል ፀጉርና ቆዳ የሚያጠቃ በሽታ ነው ይላሉ ::

እንዲሁም ቆረቆር ከአዋቂዮች ይልቅ በብዛት ዕድሜያቸው ከ3 እስከ 12 አመት ያሉ ህፃናትን ያጠቃል ብለዋል::

ዶክተር ዳዊት አዋቂወች በዚህ የራስ ቅል የፀጉር እና የቆዳ በሽታ ሊጠቁ የሚችሉት የበሽታ መከላከል አቅማቸው ከቀነሰ መሆኑን ነግረውናል ።

የቆረቆር በሽታ ምልክት

1.የራስ ቅል ፀጉር መመለጥ
2.የሚያፈከፈሰክ ነጫጭ ነገሮች መውጣት
3.በራስ ቅል ላይ መግል መያዝ

# የቆረቆር በሽታ ምርመራ
_ ከቦታው ላይ ተፈቅፍቆ ተወስዶ በማይክሮስኮፕ ከታየ ቡሃላ ህክምና ይደረግለታል ብለዋል።

# ህክምና
_የቆረቆር በሽታን ለማከም በሚቀባ መድሀኒት ብዙ ጊዜ ላይድን ስለሚችል ቢጠቀሙት የተሻለ የሚሆነው ቢያንስ ለአንድ ወር የሚዋጥ የፈንገስ መድሃኒት በባለሙያ ትዕዛዝ በመውሰድ መሆኑን ገልፀዋል ።

_መግል ከያዘ የፀረ ባክቴሪያ መድሀኒት ያስፈልጋል በተጨማሪም መግል ከያዘ ምንም አይነት ቅባት አለመቀባት ይመከራል ይላሉ ዶክተር ዳዊት ዮሐንስ ።

የቆረቆር በሽታን ለመከላከል

_ማንኛውም ሰው ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ የሚተላለፍ በመሆኑ አንድ ሰው በተጠቀመበት ማበጠሪያና ያለመጠቀም አንደኛው መከላከያ መንገድ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አንድ ልጅ ያረገውን ኮፍያ አለመጠቀም እና ሁሉም ለየብቻ የራሱን መጠቀም አስፈላጊነው ተብሏል ።

_ልፊያ ወይንም ጭንቅላት ለጭንቅላት አለመነካካት ልጆች በትምህርት ቤት በዋናነት በሽታውን ለመከላከል ይረዳል ።

_ በተለይ ትምህርት ቤቶች ላይ ችግሩ ከልጅ ወደ ልጅ በቀላሉ ስለሚተላለፍ ህፃናትን ጭንቅላታቸውን ማየት እና የዚህ የራስቅል የፀጉር ፈንገስ ወይንም የቆረቆር ምልክት ካለባቸው መምህራን ልጆቹ እንዲታከሙ ለተማሪዎቹ ወላጆች መናገር አለባቸው።

በመጨረሻም በተለይ ደይ ኬር (day care ) የሚገቡ ህፃናት እዛው የሚተኙ ከሆነ ልጆች በጭንቅላታቸው እንዳይነካካ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው ሲሉ በጥላ የቆዳና የአባላዘር ልዩ ክሊኒክ የቆዳና የአባላዘር ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶክተር ዳዊት ዮሐንስ ለጣቢያች ሃሳባቸውን አጋርተዋል።

በልዑል ወልዴ

መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply