You are currently viewing ስለ #ብፁዕ_አቡነ_ናትናኤል እውነተኛ እረኝነት ለመመስከር ከአቡነ ሳዊሮስም ሆነ ከአቡነ አብርሃምም ጎን መሰለፍ እንደሌለብኝ አምናለሁ  ዲ/ን ብዙአየሁ ተስፋዬ  በብፁዕ አቡነ ናትናኤል በሚመ…

ስለ #ብፁዕ_አቡነ_ናትናኤል እውነተኛ እረኝነት ለመመስከር ከአቡነ ሳዊሮስም ሆነ ከአቡነ አብርሃምም ጎን መሰለፍ እንደሌለብኝ አምናለሁ ዲ/ን ብዙአየሁ ተስፋዬ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል በሚመ…

ስለ #ብፁዕ_አቡነ_ናትናኤል እውነተኛ እረኝነት ለመመስከር ከአቡነ ሳዊሮስም ሆነ ከአቡነ አብርሃምም ጎን መሰለፍ እንደሌለብኝ አምናለሁ ዲ/ን ብዙአየሁ ተስፋዬ በብፁዕ አቡነ ናትናኤል በሚመራው በም. ሸዋ ሀገረ ስብከት ቅጥረኛ ሠራተኛ ነኝ። ያደኩበት፣ አፍ የፈታሁበት ወንጌልን ከሥነ ምግባር ተምሬ ለእግዜር ሰላምታ የማልበቃው ወራዳ በክብር ሰገነት ላይ እንድቆም ያደረገኝ ምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት ነው። ምንም ከኦሮሞ እናትና አባት ብወለድም አፌን በአማርኛ ፈትቼ ኦሮምኛ ቋንቋንየለምድኩት በኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አውደ ምሕረት እንደሆነ የጉደር፣ የኮልባ፣ የሙቱሉ፣ የሌንጫ፣የአምቦ እና አከባቢው ምዕመን ሕያው ምስክር ነው። እንደ ሥጋዊ ሰው በደልን ልቁጠር ብል በአቡነ ናትናኤል በሚመራው ሃገረ ስብከት ተበድያለሁ ብዬ አምናለሁ፤ በስብከተ ወንጌል ኃላፊነት ከምሰራበት ከአምቦ መንበረ ጵጵስና መሠረተ ሕይወት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ዘረኝነት ላሰከረው ግንበኛ አድልተው የጎበዝ አለቆች በግፍ አሳደውኛል፤ በምወዳት ደብር ዳግም እንዳልቆም እንደወንጀለኛ ተሳድጃለው። እንደ ሥጋዊ ሰውበደል ልቁጠር ብል ከ4 ወራት በላይ ያለ ሥራ እና ደመወዝ ስቀመጥ የተናገረልኝ የሃገረስብከት የመምሪያ ኃላፊ የለም። ነገር ግን ከሥጋ መወለዴ የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ አላደረገኝም ከመንፈስ መወለዴ ግን የመቅደሱ ሠራዊት አድርጎኛል፤ እንደመንፈሳዊ ሰው፣ የመንፈስን አሳብ አደንደሚያስብ ወንጌላዊ ግን በቅርበት ስለማውቃቸው ስለ ብፁዕአቡነ ናትናኤል እመሰክር ዘንድ ያስገድደኛል። የቅኔ ማኅሌቱ ፈርጥ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፤ የኦሮምኛ ቅዳሴው ጌጥ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፤ የኦሮምኛ ትምህርተ ወንጌሉ ቆራጥ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል . . . ብፁዕነታቸው ከሚመሩት አኅጉረ ስብከት መካከል ምዕ.ሸዋ አንዱ ነው፤ /ከአስኮ እስከ ባኮ/ የኦሮምኛ አገልግሎት በተለይም ቅዳሴ ሰሞን ተመድቦለት የሚሠራው የአቡነ ናትናኤል ምዕ. ሸዋ ነው /ወለጋን ጨምሮ/። ወደ ሃገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ለሠራ ቅጥርም ሆነ ዕድገት ጎራ የሚል ባለ ጉዳይ የመጀመሪያው ጥያቄ “ኦሮምኛ ትችላለህ?” የሚለው ነው። የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ስዩማን /የነገሌ ቦረናው ሊቀ ማዕምራን/ ግርማ ቤጊ ወዬሳም መቅደስ ቢገቡ ብጥር ቀዳሽ፤ ቅኔ ማኅሌት ቢቆሙ ሊቅ መሪጌታ፤ ዐውደ ምሕረት ላይ ብርቱ ወንጌላዊ የኹለቱም ቋንቋ እሳት አገልጋይ ናቸው። ምክትል ሥራ አሥኪያጁ ሊቀ ኅሩያን ታምሩ እሸቱ የዘመናት የቅድስት ቤተክርስቲያን ባለውለታ ስለ ወንጌል ሁሉን የከፈሉ ከፈረስ ከመኪና አደጋዎችን ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያስተናገዱ ናቸው። ዋና ጸሐፊው መጋቤ ትፍሕት አክሊሉ ባለብዙ ትኅትና የሁለቱም ቋንቋዎች እሳት የላሰ ወንጌላዊ። የስብከተ ወንጌል መምሪያው መጋቤ ሐዲስ ጌትነት በቋንቋ አገልግሎት አብሮትማን ይሰለፍና። በበሳል ወንጌላውያን ባለ ብዙ ቋንቋ አገልጋይ የተዳረጀው የምዕ. ሸዋ ሃገረ ስብከት ጽ/ቤት ያለ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል በሳል አመራር መች እውን ይሆናል። ብፁዕ አባቴ ስለማሳነሴ ይፍቱኝ!!! ቡራኬዎ ይድረሰኝ

Source: Link to the Post

Leave a Reply