ስለ አንጋፋው አትሌት ኃይሌ ገብረ-ስላሴ ያለው መረጃ፡-እኔ ላይ የትራፊክ አደጋ እንደደረሰ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው ” – አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ፡፡አንጋፋው አትሌት ኃይሌ ገብረስ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/UIvLflKysndFRXdkDyhdlKEufs31qcgY2yPD3gYfV077Im8FApC0rJlC2YzkflGHc9zs6uwc09rj4zmnzPcn9ayeyzKJKIofeu5P4bFDnEW92E5imHyLoiCS3841oi4VqCoX4imvQQn_mXtpQoEWXOv4yX2vJcsNouKPTDKHQD7Y6gUWXeOhVt6f-DRteI9Pj1cQ09wCG5eZWJUerB5dwrLXEe9sQOHbfCRSWXac2ghUsYj8IyjociU5EpqXb4zQwg7PaECIk2P8nsEqRaCSSATYo-txYRMA_EnXGQ6CzwAzIlP_5-9-s5uUjRblTEneJZkAC8u0uLU0PBl6fstXzg.jpg

ስለ አንጋፋው አትሌት ኃይሌ ገብረ-ስላሴ ያለው መረጃ፡-

እኔ ላይ የትራፊክ አደጋ እንደደረሰ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው ” – አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ፡፡

አንጋፋው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ የትራፊክ አደጋ እንዳልደረሰበት ተናግሯል።
አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ የትራፊክ አደጋ እንደደረሰበት ሚዲያዎች እየዘገቡ ሲሆን አትሌቱ ለአል አይን በሰጠው ቃል ሀሰት ነው እኔ ላይ የትራፊክ አደጋ አልደረሰም ብሏል።
ኃይሌ ፤ “ያለንበት ሁኔታ እጅግ ከባድ ነው፣ ሌላም ነገር ቢሆን እንዲህ ነው የውሸት መረጃ የሚሰራጨው ” ብሏል።

ዛሬ ጠዋት ላይ ” ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ” በተሰኘው ሬድዮ ጣቢያ ከሚሰራጨው ” አውቶሞቲቭ ” የሬድዮ ፕሮግራም ጋር በስልክ ተደውሎልኝ ስለፍጥነት መገደቢያ ወይም ስፒድ ብሬከር ችግር መሆኑን አስተያየት ሰጥቼ ነበር ያለው ኃይሌ ፤ ” ይህ ማለት ግን ዛሬ በእኔ ላይ የትራፊክ አደጋ ደርሶብኛል ማለት አይደለም ” ሲል ተናግሯል።
አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ፤ በተሰራጨው ሀሰተኛ ዘገባ ምክንያት ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ አሳስቧቸው እጅግ ብዙ የስልክ ጥሪዎች እያደረሱኝ ነው ሲል ለአል ዓይን አማርኛ አገልግሎት ክፍል በሰጠው ቃል ተናግሯል።
በብስራት ሬዲዮ ከሚተላለፈው የአዉቶሞቲቭ ፕሮግራም ጋር በነበረው ቆታ የተናገረው ከታይ ተያይዟል፤ማድመጥ ትችላላችሁ፡፡

ኢትዮ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 10 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply