“ስለ ኢትዮጲያ አካሉን ለሰጠ ባለውለታ ምንስ ቢደረግ” ገናን ለወገኔ በአሸዋ ቴክኖሎጂ በጦር ሀሎች ሆስፒታል ደምቆ ዋለ! ጥር 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአሽዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን…

“ስለ ኢትዮጲያ አካሉን ለሰጠ ባለውለታ ምንስ ቢደረግ” ገናን ለወገኔ በአሸዋ ቴክኖሎጂ በጦር ሀሎች ሆስፒታል ደምቆ ዋለ! ጥር 5 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ የአሽዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አክስዮን ማህበር ሰራተኞች እና የስራ ኃላፊዎች “ገናን ከወገኔ ጋር” በሚል መሪ ቃል በጦር ሀይሎች ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመገኘት በሆስፒታሉ ከሚገኙ ከ 400 በላይ ከሚሆኑ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ጋር የምሳ ግብዣ አካሄዱ፡፡ በዕለቱም የጦር ሀይሎች ኮንቨረንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አዛዥ ጀነራል ሀይሉ እንደሻው የመከላከያ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጀነራል ሁሉ አገርሽ ድረስ፣ አባገዳ ዋቃ ሽፋ ፣ የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶልሽን አክስዮን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል በቀለ፣ የሀይማኖት አባት የሆኑት ሀጂ ኢብራሒም ቱፋ ፣የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሐመድ ድምጻዊ ሻምበል በላይነህ አርቲስት ተስፋዬ ሲማን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የምሳ ማብላት እና የአብሮነት ፕሮግራሙ ተካሂዷል ፡፡ አሽዋ ቴክኖሎጂ በተቋቋመ በአጭር ጌዜ ውስጥ ከተሠማራባቸው የቴክኖሎጂ ስራ ዘርፎች ባላፈ የተለያዩ ማህበራዊ ኃላፊነቶችን በመወጣት የሚገኝ ተቁአም ነው። ጀግኖች የመከላከያ ሰራዊት አባሎቻችን በይቻላል መንፈስ እንዲበረቱ ሀገራቸው በጠራቻቸው ጊዜም የበኩላቸውን እንደተወጡ ለሌሎች ወጣቶችም በተሰማሩበት ዘርፍ የጽናት ተምሳሌት እንደሆኑና መሆን እንደሚችሉ የአሸዋ ተክኖሎጂ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል በቀለ በመርሀ ግበሩ ላይ መልክት ያስተላለፉ ሲሆን በፕሮግራሙም የተጋበዙ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሀይማኖት አባቶች አባገዳ እና ሌሎችም ስለሰላም አስፈላጊነት አንድነትን ስለሀገር ፍቅር እንዲሁም ብርታት እና ጥንካሬ ለሁሉም የበለጠ እንደሚያስፈለግ ከምስጋና ጋር አያይዘው መልእክቶቻቸውን በመድረኩ አስተላልፈዋል። አሸዋ ቴክኖሎጂ የዛሬ አመትም “ገናን ለወገኔ” በሚል መሪ ቃል የገናን በአል በሸዋ ሮቢት በመገኘት ተከስቶ በነበረው ጦርንት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች አስፈላጊውን የበአል መዋያ ድጋፍ በማድረግ ከዋዜማው ጀምሮ የበአል እለትን አብሮ ማሳልፉ አይዘነጋም ፡፡ የቀድሞ የሐረር ሙዚቀኞች ማህበር ስለ ሀገር ኮርኳሪ ሙዚቃዎችን በሙሉ ባንድ ሲያቀርቡ ቲም የዳንስ ቡድን ደግሞ ማንም ሰው አካል ጉዳተኝነት ሳይበግረው ማንኛውንም ነገር መስራት እንደሚችል የሚያስተምር በሙዚቃ ታጅበው የተለያዩ የውዝዋዜ ትርኢቶችን በማሣየት ጀግኖች የመከላከያ ሰራዊት አባሎቻችንን አዝናንተዋል፡፡ በመረሻም የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ማህበር ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል በቀለ ይህ ማህበራዊ ሀላፊነት እንዲሳካ በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉት የአዲስ አበባ ነጋዴዎች ማህበር ፕሬዝዳንት ለወ/ሮ ዘሀራ መሐመድ እና ለተባበሩ አካላት፣ አርቲስቶች በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply