
መላው ዓለም በእግር ኳስ ንጉሥነቱ የሚስማማበት ኤዲሰን አራንቴስ ዶ ናሲሜንቶስ በአጭሩ ፔሌ፣ ሦስት የዓለም ዋንጫዎች በማንሳት በታሪክ ብቸኛው ከመሆኑ በተጨማሪ በርካታ ግቦችንም በማስቆጠር የክብረ ወሰን ባለቤት ነው። ባለፈው ሳምንት በ82 ዓመቱ ያረፈው ፔሌ የእግር ኳስ ነገር ሲነሳ ስሙ በቀዳሚነት የሚጠቀስ እና ታሪኩ ላለፉት ስድስት አስርት ዓመታት በመላው ዓለም ሲነገር ቆይቷል። በዚህም የፔሌ አብዛኛው ታሪክ እና ገጠመኙ በስፋት ተነግሯል ቢባልም ስለኳሱ ንጉሥ ብዙም ያለተባለለቸውን አስር ጉዳዮች እነሆ።
Source: Link to the Post