ስለ ኮሌራ ወቅታዊ ሁኔታ—የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትበኢትዮጵያ ኮሌራ ወረርሽኝ ነሃሴ 1/2014 በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን ዉስጥ በሃረና ቡሉክ ወረዳ የተከሰተ መሆኑ ይታወቃል…

ስለ ኮሌራ ወቅታዊ ሁኔታ—የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

በኢትዮጵያ ኮሌራ ወረርሽኝ ነሃሴ 1/2014 በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን ዉስጥ በሃረና ቡሉክ ወረዳ የተከሰተ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ወረርሽኙ ወደ አጎራባች ወረዳዎች ፣ ዞኖች የተዛመተ ሲሆን በኦሮሚያ በባሌ ፣ ጉጂ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች 8 ወረዳዎች እና በሶማሌ ክልል ሊባን ዞን 2 ወረዳዎች ተዛምቶ በአጠቃላይ በ10 ወረዳዎች የሚገኙ 66 ቀበሌዎችን ለማካለል ችሏል፡፡

የኮሌራ ወረርሽኝ በታየባቸው ሁለቱ ክልልች በ 10 ወረዳዎች ዉስጥ ወደ 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡
ከተከሰተበት ቀን ከነሃሴ 1/2014 እስከ ጥር 22/2014 በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን 6 ወረዳዎች እንዲሁም በሶማሊ ክልል በሊባን ዞን 2 ወረዳዎች የተከሰተ ሲሆን ለበሽታው መከሰት እና መስፋፋት እንደ ዋና ምክንያት የሚሆነው የንጹህ ዉሃ አቅርቦት እና የመጸዳጃ ቤት ሽፋን አነስተኛ የሆነባቸው ወረዳዎች ሲሆኑ ይበልጥ እንዲባባስ ያደረገው አከባቢው በድርቅ የተጎዳ መሆኑ ነው፡፡

ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እና ለመከላከል እንዲሁም ወደ ሌሎች አከባቢዎች እንዳይስፋፋ በየደረጃዉ (በፌደራል፣ በክልል ፣ በዞን ፣ በወረዳ ፣ በጤና ተቋማት እና በማህበረሰብ) ደረጃ ባሉ የመንግስት ተቋምት እና አጋር ድርጅቶች ጋር በቅንጅት ጠንካራ የጋራ ርብርብ እየተደረገ ይገኛል፡፡
የህክምና አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ 14 የኮሌራ ህክምና ማዕከሎች (Cholera Treatment Center/CTC) ተቋቁመዉ ሲያገለግሉ የቆዩ እና እያገለገሉ ያሉ ማዕከላት ሲኖሩ እነሱም በበርበሬ ፣ ብጊርጃ ፣ በጎሮ እና በኔንሴቦ ወረዳዎች የገኙበታል።
በመሆኑም በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየተከሰተ ያለውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስቆም እንዲሁም የማህበረሰቡን የበሽታ ተጋላጭነት ለመቀነስ መንግስት ከአጋር የልማት ድርጅቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ስራዎችን እየሰራ በመሆኑ ወረርሽኙ የመዛመት አቅሙን በመቀነስ በሶማሊ ክልል ወረርሽኙ ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ላይ ሲገኝ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን 4 ወረዳዎች ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ተረጋግጧል፡፡

@የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ጥር 26 ቀን 2015 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply