You are currently viewing ስለ ድርድሩ እና ስምምነቱ ለየክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ገለፃ ተደረገላቸው።  ከህወሃት ጋር ተስማምቶ ለመኖር ፈቃደኝነታቸውንም ገልፀዋል። ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህር…

ስለ ድርድሩ እና ስምምነቱ ለየክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ገለፃ ተደረገላቸው። ከህወሃት ጋር ተስማምቶ ለመኖር ፈቃደኝነታቸውንም ገልፀዋል። ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህር…

ስለ ድርድሩ እና ስምምነቱ ለየክልል ርዕሰ መስተዳድሮች ገለፃ ተደረገላቸው። ከህወሃት ጋር ተስማምቶ ለመኖር ፈቃደኝነታቸውንም ገልፀዋል። ጥቅምት 25 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት ሁሉም ዜጋ ኃላፊነቱን እንዲወጣ መንግስትን ወክለው የተደራደሩት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ጥሪ አድርገዋል። የሰላም ስምምነቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የግዛት እንድነት የሚያጸና በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ለተግባራዊነቱ ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ አባልና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬደዋን ሁሴን ተናግረዋል። የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴ አባላት የስምምነቱን አጠቃላይ ሂደትና ቀጣይ ስራዎችን በሚመለከት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ለሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ-ጉባኤዎች፣ ለክልል ርእሳነ-መስተዳድሮች፣ለከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችና ለብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ገለጻ አድርገዋል፡፡ በዚህም ስምምነቱ የኢትዮጵያ ህዝቦችን የጋራ ጥቅም ባስከበረ መልኩ መጠናቀቁን ነው የተናገሩት፡፡ በአንድ ሉዓላዊ ሀገር ውስጥ ሁለት የታጠቀ ሀይል ሊኖር እንደማይችልና ህግ-መንግስታዊ ስርዓቱን ማክበር እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል ነው ያሉት፡፡ ከዚህ አኳያ ከህገ-መንግስት ውጪ ያሉ እንቅስቃሴዎች ቆመው በትግራይ ክልል በህገ-መንግስቱ መሰረት ምርጫ እኪካሄድ ድረስ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደሚቋቋምም ተናግረዋል፡፡ ያለን አማራጭ እና መፍትሄ በጋራ ተሳስሮ መሄድ ነው ያሉት አምባሳደር ሬድዋን፤ ከዚህ አኳያ ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከጉዳታቸው አገግመው ወደ ቀደመው ማህበራዊ ትስስር እንዲመለሱ በጋራ ይሰራል ነው ያሉት፡፡ የደረሰው ጉዳት የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህ አኳያ የወደሙ ተቋማትን ጨምሮ የመልሶ ግንባታ ስራዎች በጋራ ርብርብ ሊከናወኑ ይገባል ብለዋል፡፡ በተለይ የመገናኛ ብዙሃን ቁርሾዎችን ማባባስ ሳይሆን ዜጎች ከችግሩ ተምረው በቀጣይ አብሮነታቸውን አጠናክረው የሚሄዱበትን ሁኔታ መፍጠር ላይ ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሰላም ሂደቱን ለማደናቀፍ የሚሰሩ ኣካላትን ደግሞ በጋራ ማስቆም እንደሚገባም መግለጻቸውን የመንግስት የቀረቡ ሚዲያዎች ዘግበዋል። ከዛሬ ጀምሮ ህወሃትን አሸባሪ ማለት የተከለከለ ሲሆን፣ ህወሃት የመንግስት አጋር ሆኖ ይቀጥላል ማለት ነው። እንደ ቢቢሲ ዘገባ ግን ህወሃት እየተከፋፈለ መሆኑ ተነግሯል። አንዳንድ የህወሃት ጀኔራሎች ከእነ ጌታቸው ረዳ ስምምነት አፈንግጠው በውጊያው ለመቀጠል ፍላጎት አላቸው ተብሏል። በዚህ ጉዳይ ህወሃት በይፋ ያለው ነገር ባይኖርም፣ ስምምነቱን የማይቀበል የህወሃት ታጣቂ የለም እያለ መሆኑ ግን እየተሰማ ነው። በእርግጥ የሳተናው ምንጮች እንዳረጋገጡት ጦርነቱ በራያ ማይጨው ከተማ አካባቢ አሁንም እየተደረገ እንደሆነ ታውቋል። የህወሃት አክቲቪስቶችም አሁንም በድሮን ተጠቃን እያሉ ነው። በሌላ በኩል የየክልል ርዕሰመስተዳድሮች ከነጌታቸው ረዳ ጋር ተገናኝተው ሊመካከሩ እንደሚችሉም ፍንጮች መሰማት ጀምረዋል። በስምምነት ሰነዱ መሰረትም እነ ጀኔራል ታደሰ ወረደ፣ እነ ጀኔራል ምግበይ ሀይለ፣ እነ ጀኔራል አብርሃ ተስፋየ ወይም ድንኩል ከነ ጀኔራል አበባው ታደሰ ጋር በአካል ተገናኝተው ሊመካከሩ ይችላሉ። የውሸት መረጃ በመርጨት የሚታወቁት ጋዜጠኞች እና አክቲቪስቶች ጀኔራል እከሌ ተገደለ ሲሉ እንዳልነበር፣ ዛሬ ተመልሰው የሰላም ስምምነቱ ጥሩ ነው፣ ህወሃት ምርጥ ድርጅት ነው፣ አንድነት ይሻላል ማለት ጀምረዋል። ከዚህ ቀደም ጦርነት ይቁም፣ የትግራይ እና የአማራ ህዝብ አንድ ነው ሲባል የሚሳደቡ ዛሬ ተገልብጠው ቁመዋል። አቡነ ማቲያስን ሳይቀር ህወሃት ናቸው፣ ቅርስ ዘረፉ፣ ከሀገር ሊኮበልሉ ነው ሲሉ የውሸት እና የጥላቻ ዘመቻ የከፈቱ ሎሌ ጋዜጠኞች ዛሬ በዚህ አቋማቸው ላይ የሉም። ጊዜ እና መስታውት ብዙ ያሳያል። የአገዛዙ ትንፋሽ የሆነው የኢሳቱ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ከዚህ የሰላም ስምምነት አውሮፓ እና አሜሪካም ይማሩ ሲል መካሪ ሆኖ ተነስቷል። እነ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ተምረው ከሩሲያ ጋር ጦርነት ያቁሙ ሲል መክሯል። ለአብነት ጋዜጠኛ ፋሲልን አነሳን እንጂ ብዙዎች ስምምነቱን እያደነቁ፣ ህወሃትን እየመረቁ፣ ብልፅግናን እያወደሱ እነ አሜሪካ ከኛ ይማሩ እያሉ ነው። ከመጠምጠም መማር ይቅደም የሚባለው ለእንደነዚህ አይነት ሎሌዎች መሆኑ ግልፅ ነው። የጦርነት ቀስቃሾች፣ ክተት መክት፣ ተደመሰሰ ዜና ነጋሪዎች ዛሬ ነጭ እርግብ መልቀቅ ጀምረዋል። በእርግጥ ማንም ነጭ እርግብን አይጠላም። ነገርግን ነጭ እርግብን የሚወደደው አለቃህ ስለፈቀደ ብቻ አይደለም። በማንኛውም ጊዜ ለሰላም እና አንድነት የሚሰሩ ድምፆች ያስፈልጋሉ። ……………….. ዘገባው የሳተናው ሚዲያ ነው ። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply