ስለ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ሲነሳ ስማቸው ከፊት ከሚጠቀሱት መካከል ይገኝበታል፡፡

ዛሬም ድረስ ስለ ብሔር ብሔረሰቦች ሲወሳ የእርሱ ስም ሳይነሳ አይታለፍም፡፡ የዚህ ሰው ፅሁፍ የኢትዮጵያን ሁኔታ ቀይሯል ብለው የሚናገሩ አሉ፡፡ በአንፃሩ ደግሞ ይህ ሰው ስለኢትዮጵያ ብሔር ብሔርሰቦች ለመፃፍ የሚያስችል ዕውቀት የለውም በማለት ይተቹታል፡፡

በእስር በቆየባቸው ጥቂት ጊዚያት ከተገናኛቸው ሰዎች ውጪ ኢትዮጵያን ተዛዋውሮ ጎብኝቶ፤ ህዝቡን አነጋግሮም አያውቅም፤ ስለዚህ ስለብሔር ብሔረሰቦች ጥያቄ ሊያፅፈው የሚችል በቂ ግንዛቤ የለውም ይሉታል፡፡ እንዲህ በድጋፍም በንቃፍም የሚነሳው ሰው ዛሬም ብዙዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ይዘክሩታል፡፡ ባለፈው የ2013 ዓመት እንኳን እሱ የፃፈውን ፅሁፍ አስመልከቶ አንድ መድረክ ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ ከኢህአፓው ብርሃነ መስቀል ረዳም ጋር ወዳጆች ነበሩ፡፡ ይህን ሰው በዕለቱ የምናብ እንግድነት አብርሃም ታደሰ ጋብዞ አስተናግዶታል፡፡

 አዘጋጅ፡ አብርሃም ታደሰ

ቀን 28/04/2013

የምናብ እንግዳ

Source: Link to the Post

Leave a Reply