ስልጣኑንን ያለአግባብ የሚጠቀም የጸጥታ ኃይል በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን የፌደራል ፖሊስ ገለፀ፡፡

ለ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በሚደረገው ቅድመ ዝግጅት በቅስቀሳና በእጩ ምዝገባ ወቅት በመንግስት መዋቅር ውስጥ ባሉ የጸጥታ ኃይሎች ያለ አግባብ ጫና እና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው መሆኑን ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያነሳሉ፡፡

የፌደራል ፖሊስ የህግ አገልግሎት ዳይሬክተር ረዳት ኮምሽናር ፋሲል አሻግሬ እንደተናገሩት ፖሊስም ሆነ ሌሎች የጸጥታ ኃይሎች ስለፈለጉና ስላልፈለጉ ሳይሆን ጸጥታውን ማስጠበቅ ግዴታቸው በመሆኑ ከዚህ ድርጊት ሊቆጠቡ ይገባል ብለዋል፡፡

ያለአግባብ የሚቀጣ ግለሰብም ሆነ የሚቀጣ የጸጥታ ኃይል  በወንጀል የሚጠየቅ መሆኑን ረዳት ኮምሽነሩ ተናግረዋል፡፡

በተለይም ፍርድ ቤት ነፃ ብሎ ያሰናበታቸውን ተጠርጣሪዎች ፖሊስ መልሶ የሚያስርበት ወይም በእስር እንዲቆዩ ማድረጉ ተገቢነት የሌለው የፍትህ ስርዓቱን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው ብለዋል፡፡

ስልጣኑንን ያለአግባብ የሚጠቀም የጸጥታ ኃይል ወይም ፖሊስ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን  የተናገሩት ረዳት ኮምሽነር ፋሲል ፍርድ ቤት ነጻ ያለውን ፖለስ ተጠያቂ የሚያደረግበት ሁኔታ መሻሻል ወይም መስተካከል እንዳለበት በመተማመን እየተሰራ ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ቀን 04/07/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply