You are currently viewing ስልጣንዎን ለጊዚያዊ ሲቪል አስተዳደር ያስረክቡ ፓርላማውም ይበተን ሲሉ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቀረቡ።            ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም…

ስልጣንዎን ለጊዚያዊ ሲቪል አስተዳደር ያስረክቡ ፓርላማውም ይበተን ሲሉ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቀረቡ። ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም…

ስልጣንዎን ለጊዚያዊ ሲቪል አስተዳደር ያስረክቡ ፓርላማውም ይበተን ሲሉ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቀረቡ። ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ የአብን እና የምክርቤቱ አባል ለጠ/ሚኒስትሩ ያቀረቡት ጥያቄ – ጠ/ሚኒስትሩ ወደስልጣን ከመጡ ወዲህ ኢኮኖሚዉ ታሟል፣ ወጣቶች ሀገራቸዉ ዉስጥ ተስፋ በማጣታቸው ስደትን ምርጫቸዉ አድርገዋል ፣ ዜጎች በጠራራ ፀሀይ ይታገታሉ ፣ ብልጽግና መራሹ ፓርቲ ሀገሪቱ ከገባችበት ቅርቃር ማዉጣት ስለማይችሉ ስልጣኖን ለጊዜያዊ አስተዳደር እንዲያስረክቡ ሲሉ ጠይቀዋል። “ሙሉ አማራ ክልል አዲስ የጦርነት ቀጠና ሆኗል ፤ ከፊል ኦሮሚያ በተመሳሳይ የጦር ቀጠና ናቸዉ። ከ 200 ሺህ በላይ ሰዎች በመንግስት ቤታቸዉ ፈርሶ ሜዳ ላይ ወድቀዋል። እንደ ብልጽግና ሹማምንት አባባል ህጋዊ ደሃ ተደርገዋል። በሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በጦርነቱ እና በማንነት ጥቃት ተፈናቅለዋል። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል። ለዚህ ሁሉ ቀዉስ ዋነኛ ተጠያቂው የብልጽግና መንግስት እና የእርሶ(የጠ/ሚኒስተሩ ) የወደቀ አመራር ነዉ” ብለዋቸዋል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply