ስሎቫኪያ ለዩክሬን የጦር ጄት የለገሰች ሁለተኛዋ የኔቶ አባል ሀገር ሆነች፡፡

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት /ኔቶ /አባል የሆነችዉ ስሎቫኪያ ተዋጊ ጄቶችን ለዩክሬን ድጋፍ ማድረጓን አስታዉቃለች፡፡

የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር ኤዱአርድ ሄገር ፤13 ሚግ 29 የጦር ጄቶችን ለዩክሬን እንልካለን ብለዋል፡፡

ስሎቫኪያ ባላት አቅም ዩክሬንን ለመርዳት ዝግጁ መሆኗንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታዉቀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የኔቶ አባል የሆነችዉ ፖላንድ ለዩክሬን ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጓ የሚታወስ ነዉ፡፡

የጦር መሳሪያ ድጋፉን ተከትሎም ሞስኮ ሁለቱን የኔቶ አባል ሀገራት አስጠንቅቃለች ሲል ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

የክሪሚሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ የኔቶ አባል ሀገራት ጦርነቱን ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች ቢቆጠቡ መልካም ነዉ ብለዋል፡፡

በአባቱ መረቀ
መጋቢት 08 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply