You are currently viewing “ስምምነት ተደረሰ የተባለበት ሁኔታ፣ የመፈንቅለ ሲኖዶስ ጠንሳሽ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ነበሩበት አህጉረ ስብከታቸው የተመለሱበት መንገድና፣ የአብዛኛዎቹ አፈንጋጭ መነኮሳት ይቅርታ አጠያየቅ እኛን…

“ስምምነት ተደረሰ የተባለበት ሁኔታ፣ የመፈንቅለ ሲኖዶስ ጠንሳሽ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ነበሩበት አህጉረ ስብከታቸው የተመለሱበት መንገድና፣ የአብዛኛዎቹ አፈንጋጭ መነኮሳት ይቅርታ አጠያየቅ እኛን…

“ስምምነት ተደረሰ የተባለበት ሁኔታ፣ የመፈንቅለ ሲኖዶስ ጠንሳሽ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ነበሩበት አህጉረ ስብከታቸው የተመለሱበት መንገድና፣ የአብዛኛዎቹ አፈንጋጭ መነኮሳት ይቅርታ አጠያየቅ እኛንም እንደ ሌሎች ምእመናን ጥልቅ ቅሬታና ሀዘን እንዳሳደረብን ለማሳወቅ እንፈልጋለን።” ሀያ ሰባት ማሕበራት የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ግንቦት 9/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ ጉዳዩ: አዲስ ኤጲስ ቆጶሳትን ስለመምረጥና በቤተክርስቲያኒቱ ላይ የተደቀነውን አደጋ ይመለከታል እኛ፣ ስማችን ከደብዳቤው መጨረሻ የተዘረዘረው፣ በተለያዩ ዓለማት የምንገኝ የሲቪክ ማህበራት፣ በመንግሥት የሚደገፈው ስብስብ በጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም. ህገወጥ የሃይማኖት፣ የቀኖናና ህገ-ቤተክርስቲያን ጥሰት በፈፀመበት ጊዜ፣ ድርጊቱን በማውገዝ ከቤተክርስቲያን ጎን የቆምን መሆኑን የሚያሳይ ጠንካራ መግለጫ ማውጣታችን ይታወሳል። በመግለጫችንም፣ በመንግሥት የፀጥታ አካላት በግፍ ስለተገደሉ ከሃምሳ የማያንሱ ምዕመናን ፍትህ እንዲሰጥ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ቀሪ ቤተሰቦቻቸው ካሳ እንዲከፈላቸው መንግሥትን ጠይቀናል፤ የታሰሩትም እንዲፈቱ ድምፃችንን አሰምተናል። ከመግለጫውም አልፎ፣ በተለያዩ የውጭ አገራት የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት በማውገዝ በሰልፍ ተቃውሟችንን ገልፀናል፤ በየሚዲያዎች እየቀረብንም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተፈጠረውን ችግር ለማስረዳት ጥረት አድርገናል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካይነት ስምምነት ተደረሰ እስከተባለበት ጊዜ ድረስ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ ያሳየው ቆራጥና ጠንካራ አመራር አድናቆት የተቸረው እንደነበር ቢታወስም፣ በአንፃሩ ስምምነት ተደረሰ የተባለበት ሁኔታ፣ የመፈንቅለ ሲኖዶስ ጠንሳሽ ሊቃነ ጳጳሳት ወደ ነበሩበት አህጉረ ስብከታቸው የተመለሱበት መንገድና፣ የአብዛኛዎቹ አፈንጋጭ መነኮሳት ይቅርታ አጠያየቅ እኛንም እንደ ሌሎች ምእመናን ጥልቅ ቅሬታና ሀዘን እንዳሳደረብን ለማሳወቅ እንፈልጋለን። እርቅ ተፈፀመ ከተባለም በኋላ፣ ምዕመናንን ማሰሩ፣ ማዋከቡና፣ ከሥራ ማባረሩ እንደቀጠለ ከመሆኑም በላይ፣ የቤተክርስቲያኗ ንብረቶች ንዋየ ቅዱሳት በህገ-ወጡ ቡድን እየተዘረፉ መሆናቸው በገሃድ ሲታወቅ፣ ከቤተ ከህነቷ የሚጠበቀው ተቃውሞ አለመታየቱ፣ ቅሬታችንን የበለጠ የከፋ አድርጎታል። ይህ በእንዲህ እያለ፣ አሁን እየተካሄደ ባለው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ፣ አብዛኞቹ አፈንጋጮቹ የጵጵስና ሹመት እንዲሰጣቸው በመንግሥት በኩል ከፍተኛ ሴራ መሸረቡና፣ በእናንተ በብፁአን አባቶች ላይም ከፍተኛ ጫና እየተደረገባችሁ መሆኑን ከውስጥ ምንጮች በተጨባጭ ለመረዳት ችለናል። መንግሥት ገና ከጅምሩ፣ በፖሊሲ ደረጃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን የዕድገት ፀር ናት ብሎ በመፈረጅ ለማዳከም፣ ብሎም ለማጥፋት ቆርጦ መነሳቱ በግልጽ የሚታወቅ ስለሆነ፣ አሁን ይህን መሰል ድርጊት እየፈፀመ መገኝቱ የሚገርም ነገር አይሆንም። ለዚህ አብነትም፣ ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ የተቃጠሉ ከ50 በላይ አብያተ ክርስቲያናት፣ ቁጥራቸው ከፍ ያለ የወደሙ ገዳማት፣ እንዲሁም በሺህዎች የሚገመቱ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ካህናትና ምዕመናን እንዳሉ ማስታወሱ በቂ ነው። አሁንም በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ ዘርፈ-ብዙ ዘመቻ የከፈተባት ሲሆን፣ በዐማራው ሕዝብ ላይም ግልፅ ወረራ በማወጅ፣ አረመኒያዊ ጭፍጨፋውን እያደረገ ይገኛል። ከ40 ሺህ በላይ ዐማራወችንም አስሮአል፤ ከ35 ሺህ በላይ የዐማራ ተወላጅ ቤቶችን አሁን ሸገር ብሎ በሰየመው ከተማ አፍርሶ፣ ቢያንስ ከ300 ሺህ በላይ ህዝብ እንዲፈናቀል እድርጎአል። ብፁዓን አባቶች፣ ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና በዐማራው ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለው መጠነ-ሰፊ ዘመቻ የማይነጣጠልና የታቀደ መሆኑን ትስቱታላችህ ብለን አናምንም። ዋናው ማሳሰቢያ፣ እየተካሄደ ያለውን ዘመቻ በተናጠል ባለማየት፣ ምዕመኑ በአንድነት በመሆን ራሱን፣ ሃይማኖቱንና ኢትዮጵያን መጠበቅ እንዲችል ከዚህ በፊት እንዳሳያችሁት ጠንካራና ብቃት ያለው ሃይማኖታዊ አመራር፣ አሁንም እንድትሰጡ ነው። በተለይም፣ አሁን የምታሳልፉት ውሳኔ፣ የኦርቶዶክስ ሃይማኖትን ቀጣይ አቅጣጫ መተለም ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን እንደ አገር ማስቀጠል ላይ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አለው ብለን እናምናለን። ስለዚህ፣ ውሳኔ ላይ ክመድረሳችሁ በፊት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም ሆነ አገራችን ከገጠማቸው ፈተና ለመሻገር እንዲችሉ ሊረዱ ይችላሉ ብለን የገመትናቸውን፣ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በፅኑ ግንዛቤ እንድታስተናግዱ በአክብሮት እናቀርባለን 1.ቤተክርስቲያንም ሆነ ምዕመኑ ፣ በየአቅጣጫው የተከፈተበትን ዘመቻ ለመከላከል እየተዋከበ፣ እየተገደለ፣ እየተፈናቅለ፣ እየታሰረ፤ ብሎም እየተሳደደ ባለበትና ፍፁም ባልተረጋጋበት ሁኔታ፣ በአጀንዳ የተያዘው የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ ሕዝበ-ምዕመኑም ሆነ አገር እስኪረጋጋ እንዲዘገይ፤ 2. በሁሉም የቤተክርስቲያኗ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊነት ተዘጋጅቶ የቀረበው የኤጲስ ቆጵሳት ቅድመ ምልመላ መሥፈርቶች የያዘው ሰነድ ለሲኖደዶሱ ምልዐተ ጉባኤ ቀርቦ ተመርምሮ ሳይፀድቅ ምንም አይነት አዲስ የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንዳይካሄድ፣ 3. ሃይማኖትን፣ ቀኖናንና ህገ-ቤተክርስቲያንን በመጣስ በህገ-ወጡ የኤጲስ ቆጶስነት ሹመት ተካትተው የነበሩ ሃያ አምስት መነኮሳት በሙሉ መቸውንም ቢሆን ለኤጲስ ቆጶስነት ማዕረግ እንዳይበቁ፤ 4. መንግሥት አሁን ያዘጋጃቸው ካልተሾሙለት ሌሎችን ለሹመት ማቅረቡ ስለማይቀር፣ በምንም አይነት በመንግሥት ግፊት የሚቀርብ ግለ ሰብ በየትኛውም ደረጃ ላለ የቤተክርስቲያን እለቅነት እንዳይሾም፤ 5. ከተለያዩ የቤተክርስቲያኗ ማህበራት ሊቃውንት እየቀረበ ያለው የቤተክርስቲያንን አስተዳደር ዘመኑን የዋጀ ለማድረግ የሚያስችሉ ጥናቶች ተመርምረው በመፅደቅ ወደ ሥራ እንዲገቡና፣ በመጨረሻም፤ 6. በዐማራው ሕዝብ ላይ በመንግሥት ቀጥተኛ ትእዛዝ የሚካሄደውን ጦርነት፣ ጭፍጨፋና መፈናቀል በቅዱስ ሲኖዶሱ ምልአተ ስብሰባ ተምርክሮበት፣ ያለምንም ማመንታትና ፍራቻ አጥብቃችሁ እንድትቃወሙና እንድታወግዙ፣ እንዲሁም ይህንን መንግሥታዊ የወንጀል ድርጊት ለማስቆምና ለመከላከል፣ ኃይማኖታዊ ጥሪ ለመላው አገራዊና ዓለም አቀፋዊ የእምነት ተከታዮች በአስቸኳይ እንድታስተላልፉ። ቸሩ እግዚአብሔር ቅድስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን፣ ብሎም ቅድስት አገራችንን ኢትዮጵያን ከገጠማቸው ፈተና እንዲያሻግራቸው እንማፀናለን! ፈራሚ ድርጅቶች፦ SIGNATORY ORGANIZATIONS 1. Abba Bahrey Forum 2. Adwa Great African Victory Association (AGAVA) 3. All Shewa Ethiopian People Multipurpose International Association 4. Amhara Association in Queensland, Australia Amhara Dimtse Serechit 5. Amhara Wellbeing and Development Association 6. Communities of Ethiopians in Finland 7. Concerned Amharas in the Diaspora 8. DC Task Force 9. Embilta Forum 10. eT-Hub 11. Ethio-Canadian Human Rights Association 12. Ethiopian American Development Council (EADC) 13. Ethiopian Community Association of Greater Cincinnati (ECAGC) 14. Ethiopian Dialogue Forum (EDF) 15. Ethiopiawinnet – Council for the Defence of Citizen Rights (E-CDCR) 16. Freedom and Justice for Telemt Amhara 17. Global Alliance for Justice – The Ethiopian Cause 18. Global Amhara Coalition (GAC) 19. Gonder Hibret for Ethiopian Unity 20. Major Lemma Woldetsadik Memorial Foundation 21. Network of Ethiopian Scholars (NES) 22. Radio Yenesew Ethiopia 23. Selassie Stand Up, Inc. 24. The Ethiopian Broadcast Group 25. Vision Ethiopia (VE) 26. Welkait, Tegede, Telemt, Setit Humera Global Amhara Unity Association 27. Worldwide Ethiopian Civic Associations Network (WE-CAN)

Source: Link to the Post

Leave a Reply