ስብሃት ነጋ ተያዙየጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የጥፋት ቡድኑ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ገለፀ።እነዚህኑ የጁንታው አመ…

https://cdn4.telesco.pe/file/MvteoY9JL0eJH4oGsPTKS93MqoZe3TYQuEoe_y2vxbT06x4zZ5z9M9pwzqlsUAAS1NGZs_zuy1GQxApSZYMDAW8CJH5EWRJWpo9dyUVBz_4D7GtJNvLXVjSBy4tmmc5LNhSBDvzN9aqE7lfjsV1fRZDIHjWW7aY16OnF-skrixoFhyJsxkB-XaS8R1iFm5UAYhz5P2XDa29cKBsXNqWuVlCNeQMUrg0WhbDftG0C4WZlUGOitkTzMOkR-aWREuI8mg0j7LzazHA0KoEMCxTnES-wymkNsVNDECnnmmsYrFoF_F-BAHdSqSC9nbAtRFUmlxb0pLFgREkBT47tuTZyVA.jpg

ስብሃት ነጋ ተያዙ

የጥፋት ስትራቴጂስቱና ዋነኛው የጁንታ መሪ ስብሃት ነጋን ጨምሮ ሌሎች የጥፋት ቡድኑ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ገለፀ።
እነዚህኑ የጁንታው አመራሮች ለመከላከል በአካባቢው ጥበቃ ላይ የነበረ የጁንታው ታጣቂ ሀይልም መደምሰሱን ተናግረዋል።
በቁጥጥር ስር የዋሉት፣
1. የጁንታው ቁንጮ አመራርና የጥፋት ስትራቴጂስት፣ ስብሃት ነጋ፣
2. ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሃት ነጋ ባለቤትና ቀደም ሲል በጦር ሃይሎች ሆስፒተል ሃኪም የነበረች፣ በኋላም በጡረታ የተገለለች፣
3. ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ- ከመከላከያ የከዳ፣
4. ኮሎኔል የማነ ካህሳይ- ከመከላከያ የከዳ፣
5. አስገደ ገ/ ክርስቶስ- ከመሃል ሀገር ተጉዞ ቡድኑን የተቀላቀለና ለጊዜው ሃላፊነቱ ያልታወቀ ግለሰብ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን
6. የሜጀር ጀነራል ሃየሎም አርአያ ባለቤት የነበረችና ኑሮዋን በአሜሪካ አድርጋ የቆየች በኋላም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ወደ ጁንታው ተቀላቅላ የነበረች፣ ወይዘሮ አልጋነሽ መለስ ጁንታውን በመያዝ ኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ ለማምለጥ ስትሞክር ገደል በመግባት ህይወቷ ማለፉን የመከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዴር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ገልፀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply