You are currently viewing ስናይፐር እና ዲሽቃ የጠመዱ የገዢው ቡድን ወታደሮች የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎችን እያሸበሩ ነው ተባለ።       አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሰኔ 28/2015 ዓ/ም_ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ…

ስናይፐር እና ዲሽቃ የጠመዱ የገዢው ቡድን ወታደሮች የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎችን እያሸበሩ ነው ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሰኔ 28/2015 ዓ/ም_ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ…

ስናይፐር እና ዲሽቃ የጠመዱ የገዢው ቡድን ወታደሮች የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎችን እያሸበሩ ነው ተባለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ሰኔ 28/2015 ዓ/ም_ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በከተማዋ በአሁን ሰዓት የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ እንቅስቃሴ እንዲቆም የተደረገ ሲሆን ከዚህ አልፎ የንግድ ተቋማት እንዲዘጉ ተደርገዋል ሲሉ ነዋሪዎቹ ገልፀዋል። ሰኔ 27/2015 ዓ/ም በሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ባልታወቁ አካላት ከተገደሉ በኋላ ነው በከተማዋ የባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪ ባጃጅ እና የንግድ ተቋማት እንቅስቃሴ እንዲቆም የተደረገው ተብሏል። በኃላፊው ግድያ ምክኒያት የከተማ አስተዳደሩ የጊዜያዊ ጸጥታ ኮማንድ ፖስት በሰጠው መግለጫ ከዛሬ ሰኔ 28/2015 ዓ/ም ጀምሮ ከምሽቱ 12:00 ስዓት በኋላ ማንኛውም ተሽከርካሪ ይሁን የሰው እንቅስቃሴ ላልተወሰነ ጊዜ ሙሉ በሙሉ የተገደበ መሆኑን አሳውቋል። አስቸኳይ አዋጁ ከምሽቱ 12 ሰዓት በኋላ እንቅስቃሴን የሚገድብ ቢሆንም ነገር ግን ከማለዳው ጀምሮ የንግድ ተቋማት እንዳይከፈቱ፣ ባጃጆችም ወደ ስራ እንዳይገቡ የከተማዋ ሚሊሾች አግደዋል ነው የተባለው። የገዢው ቡድን ወታደሮች ዛሬ ከማለዳው ጀምረው በከተማዋ የተለያዩ ቦታወች ላይ ድሽቃ እና ብሬን አጥምደው በመዋል ህዝቡን እያሸበሩ እንደሆነና በዚህም መጠነኛ ውጥረት መንገሱን ነው የከተማዋ ነዋሪዎች የገለፁት። በተጨማሪም እነዚህ ወታደሮች በከተማዋ በመንቀሳቀስ የሚያገኟቸው ሰዎች ላይ ድብደባና ወከባ እየፈፀሙ ስለመሆኑ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ የዘገበው የአማራ ድምፅ ሚዲያ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply