You are currently viewing ስንደጋገፍ ያምርብናል! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ሚያዝያ 15 ቀን 2014 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ የክፋት እና የክፉዎች ማርከሻው በጎ ተግባርንና በጎ ሰሪዎችን ማብዛትና ማበ…

ስንደጋገፍ ያምርብናል! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የክፋት እና የክፉዎች ማርከሻው በጎ ተግባርንና በጎ ሰሪዎችን ማብዛትና ማበ…

ስንደጋገፍ ያምርብናል! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የክፋት እና የክፉዎች ማርከሻው በጎ ተግባርንና በጎ ሰሪዎችን ማብዛትና ማበረታት ነው። መደጋገፍ ሰዋዊ እና ተፈጥሮአዊ ነው፤ ለሰው ሰው ነው ልብሱ፤ ለወገን ደራሽ ወገን ነው የሚባለውም በችግርም ሆነ በደስታ ጊዜ ሰው ከሰው መገናኘት፣ መጠያየቅና መደጋገፍ ያለ፣ የነበረና የሚኖር ነው። የውብዳር ወንድሙ ትባላለች፤ በጎፈ ቃደኛ ናት። ከሰሞኑ ከአሜሪካ ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ በመመለስ ወደተለያዩ አካባቢዎች በማቅናት በተለያዩ ጊዜያት ጾታዊ ጥቃት የደረሰባቸውን እህቶችን በግሏ በአካል በማግኘት ለማነጋገር፣ለማሳከምና ለመደገፍ አቅዳለች። በማንነታቸው ብቻ ለዘመናት ከሚኖሩበት ቀዬ ተፈናቅለው ለተቸገሩ ወገኖቻችንም የድርሻውን እያበረከተች ነው። ከተቸገሩ ወገኖች ጎን በመሆን መደገፍ ዛሬ አልጀመረችም፤ ይልቁንስ በተለያዩ ጊዜያት ለበርካታ ተጎጅዎችና አቅመ ደካሞች በመድረስ ረገድ ወገናዊ ኃላፊነቷን በመወጣት የምትታወቅ ናት። በተለይም በጦርነት ወቅት ኃላፊነት በማይሰማቸው የአሸባሪው ትሕነግ አባላት በኃይል እና በቡድን የተደፈሩ አካላትን በማሳከም እና በመደገፍ በኩል የሄደችበት ርቀት የሚገርም እና የሚመሰገን ነው። ማንነት፣ሀይማኖት፣ ቋንቋንና ሌላም ነገር ቆጥሮ በጥላቻ እና በሀሰት ትርክት ነሁልሎ በኋላቀርነት ስሜት የሚገድል፣ የሚያፈናቅልና የሚዘርፍ ሰዋዊ አውሬ በበዛበት ዘመን መልካምነትን፣ደግነትንና ሰውነትን የበለጠ ገንዘቡ አድርጎ የሴረኞችን ክፉ ተግባር በማውገዝ የተሰበረን ልብ በሚችሉት መንገድ ለመጠገን የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ሊበረታታ ይገባዋል። አሳዳጊ አልባ ህጻናትን በኃላፊነትና በተቆርቋሪነት ስሜት ከማሳደግ ባሻገር በጦርነት ምክንያት ባላቸውንና አባታቸውን ያጡ እንዲሁም ሆንተብሎ ለተገደለባቸው እህቶቻችን ጥንድ የእርሻ በሬዎችንና በጎችን ገዝተው እስከመስጠት ደርሳለች። እግረ መንገዷንም የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ቦነያ ቦሼ በማንነታቸው የተፈናቀሉ የተወሰኑ አማራዎችን ወደ አዲስ አበባ ዙሪያ ወለቴ አጃምባ በመሄድ ጎብኝታለች። በዚህም በአካባቢው ላገኘቻቸው 5 ተፈናቃዮች ማለትም:_ 1) ባዬ አጥናፌ/ ፋሲካ መጨያው፣ 2) ደሳለች መጨያው፣ 3) መርጌታ ልዑል በላይ፣ 4) አቢ አያሌው እና 5) ምትኬ ያየሰው ለተባሉ ወገኖች ለእንዳንዳቸው 1 ሽህ ብር ከመስጠት ባሻገር በጣም የተጎዱ፣ የወለዱ እና በእድሜ የገፉ እናቶችን ጭምር በማካተት ለ5 ሰዎች በቀጣይ በዘላቂነት በየወሩ ለእያንዳንዳቸው 6 ሽህ ብር ለመስጠት ቃል ገብታለች። ከመካከላቸው ለ3ቱ የ3 ወር የቤት ኪራይ በወር 6 ሽህ ብር ለአንድ ሰው 18 ሽህ ብር በድምሩ 54 ሽህ ብር በአካውንታቸው አስገብታለች። በየወሩ 6 ሽህ ብር የሚረዱ ወገኖችም:_ 1) ወ/ሮ ዘውዴ ሰጥቶ ጌጡ፣ _ከወራት በፊት ጀምራ ስታግዛት የቆየች ከሁለት ወር በፊት የወለደች፣ 2) ወ/ሮ ማረች አየነ፣ _አካል ጉዳተኛ እና በእድሜ የገፉ እናት፣ 3) ወ/ሮ ጥሩሰው ጸጋዬ፣ _በእድሜ የገፉ እና አካል ጉዳተኛ የሆኑ እናት፣ 4) አቶ ጌታሁን ታረቀኝ (የእድሜ ባለጸጋ) እና አቶ ተመቸው አደፍርስ_8 ቤተሰብ ያላቸው፣በየወሩ ገቢ የሚደረግላቸው 9 ሽህ ብር፣ 5) መርጌታ ልዑል በላይ፣ _ሀብት ንብረታቸውን ጥለው ከእነ ቤተሰቦቻቸው የተፈናቀሉ፣ በአጠቃላይ እህታችን የውብዳር ለተጎዱ ወገኖቻችን እንዲህ ዓይነት አርዓያነት ያለው የሰብአዊ እርዳታ ማድረጓን አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በስፍራው ተገኝቶ አረጋግጧል፤ ስንደጋገፍ ያምርብናል በዚህም ለመልካም ተግባሯ ከልብ ልትመሰገን ይገባታል ለማለት ይፈልጋል። በእርግጥም እያንዳንዱ ዜጋ በዚህ መልኩ ወገናዊ ኃላፊነቱን መወጣቱ አበረታች ነው። መንግስት መንግስታዊ ኃላፊነቱን በሚገባ ካለመወጣቱ አንጻር እየመጡ ያሉ በርካታ ሀገራዊ ችግሮች አሉ፤ በተለይ የጅምላ ፍጅቱና መፈናቀሉ በተለይም በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ደርሰዋል። ለክፉዎችና ለአፈናቃዮች ልቦና ይስጥልን! መልካም እና ደጋግ ሰዎችን ፈጣሪ ያብዛልን!

Source: Link to the Post

Leave a Reply