ስኪልማርት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎችን አስመርቋል።ኮሌጁ በሁለት የማስተርስ መርሀ-ግብሮች ማለትም በአካውንቲንግና ፋይናንስ እና…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/sV5oWorafCz8iegCD_PMjHpv6xOmwdx8bX2bUiA7Hi0-hOn_zVqVGdNFKVCY_D8X-ttL2RqhixlqoKJhAtZuzBi3w-R7S6E2IX0oTO9OTFACe0qwQv04_SJOdySAtdEyGADbbb-_GdT3zPBStRoZXA_D06F3SK3aG14NKpT-YrencFoYClLtVJ9se97k_ppRF6QP4HGfwNiVJcUIfYSTcCwxDDNSngD1st1PPvqwI6dtDxo1R05Dp3NVpraxDc8GUMa2dWcuGH3DJf5AT-5yGjWuZA-lcqygkludXv0xTETnF9h2WksVmowNDzEaXDUhpE4OIxJ10oyzX7Hwy08bGg.jpg

ስኪልማርት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያ ዙር ተማሪዎችን አስመርቋል።

ኮሌጁ በሁለት የማስተርስ መርሀ-ግብሮች ማለትም በአካውንቲንግና ፋይናንስ እና በፕሮጀክት ማናጅመንት አናሊሲስ ኤንድ ኢቫሉዌሽን ፕሮግራሞች በቀንና በማታው መርሀ ግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቀዩ 312 የድህረ-ምረቃ ተማሪዎችን ነው በትናንትናው እለት ያስመረቀው።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የቢዝነስ ባለሙያው ዶ/ር ወረታው በዛብህ ባስተላለፉት መልዕክት ተመራቂዎች በኮሌጁ ቆይታቸው ከቀሰሙት እውቀት ባሻገር ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ጠቁመዋል።

ክህሎት ትጋት ነው፣ለሙያ ሰነ ምግባር ተገዥ መሆን ነው፣ለራስ-ለዓላማ መታመን ነው ያሉት ዶ/ር ወረታው ተማሪዎችም የቀሰሙት እውቀት የተሻለ ፍሬ የሚያፈራው ክህሎት ሲታከልበት እንደሆነ ገልጸዋል።

የስኪልማርት ትምህርት ልማት አክስዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ በቀለ ምንዳ በበኩላቸው ኮሌጁ ባለፉት ሶስት አመታት በድህረ ምረቃ ዘርፍ ትኩረት አድርጎ በሀገሪቱ ያለውን የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ የበኩሉን አስተዋፆ ለማበርከት ወደ ዘርፊ መቀላቀሉን ገልጸዋል።

በትናንትናው እለትም ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ካምፓስ ያስተማርናቸውን ተማሪዎች ለምርቃት ማብቃቱን ገልጸዋል።

ኮሌጁ በአሁኑ ሰዓትም በአዲስ አበባ መገናኛ አደባባይ እና በባህርዳር ከተማ በሚገኙት ሁለት ካምፓሶቹ የማስተርስ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ተመራቂ ተማሪዎች ከሰሯቸው የመመረቂያ ጥናታዊ ጽሁፎች መካከል ተግባራዊ ቢደረጉ ችግር ፈቺ ይሆናሉ ተብለው የተመረጡ 3 ጥናታዊ ጽሁፎችን ያዘጋጁ ተመራቂዎች የገንዘብና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply