ስኬታማ ሴቶች ለወጣት ሴቶች ልምድ የሚያካፍሉበት መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

ስኬታማ ሴቶች ለወጣት ሴቶች ልምድ የሚያካፍሉበት መርሐ ግብር ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፈው አመት የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ስኬታማ ሴቶች ለወጣት ሴቶች ልምድ የሚያካፍሉበት መርሐ ግብር ይፋ ሆኗል፡፡

በሴቶች፣ ሕፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር የተዘጋጀው መርሐ ግብር የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በተገኙበት ነው ይፋ የሆነው።

በሸራተን አዲስ ይፋ የሆነው መርሐ ግብር ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ የዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎችን ከስኬታማ ሴቶች ጋር በማጣመር በስልጠና ማብቃት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፌልሰን አብዱላሂ የዩኒቨርሲቲ ሴት ተማሪዎችን በመምከርና በመደገፍ የሚደርስባቸውን ተጽዕኖ ተቋቁመው ወደ አመራርነት እንዲመጡ ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

የተመረጡት ተማሪዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች ስኬታማ የሆኑ ሴቶች ልምዳቸውን እንደሚያካፍሏቸው የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ስኬታማ ሴቶች ለወጣት ሴቶች ልምድ የሚያካፍሉበት መርሐ ግብር ይፋ ሆነ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply