ስዊድንና ፊንላንድ ከቱርክ በኩል የገጠማቸው ተቃውሞ ለውጥ እያሳየ እንደሚገኝ ዲፕሎማቲክ ምንጮች ገለጹ፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ሃገራቱ ለኔቶ አባልነት ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ‹‹ እንዴት…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/o6vCp-QAQFuxdnd6bHeqwWGfde_d1pxe5EBJzBeEtztR13Yx27x16g_-aQJdCuwmvo4E8Yp8bDLOC-4uoyqkJqyYSAPacYNxhBtRZFsUEUe-VddU7DZ03ky_bgc4ZpJnaItRs3HNi0NJ4lZUTXVSilLOKUJjkPYbuOxvHUmQA-1tq2oyesL2mRmJYSHBEP4AUQRmrE7cm-q6bNX2M8gR9s0NJn2-mW3VvH-s4az0LumG9DuaW2TB6CQscpf9sBYgmB0oLroEZPD5yC4ySFTO4tq_k8XmlUzMLwmbUoqlQyfil2MrMIpcWDHOZT2FWo6ffho9Igzdab0r0cayVRiLZQ.jpg

ስዊድንና ፊንላንድ ከቱርክ በኩል የገጠማቸው ተቃውሞ ለውጥ እያሳየ እንደሚገኝ ዲፕሎማቲክ ምንጮች ገለጹ፡፡

ባሳለፍነው ሳምንት ሃገራቱ ለኔቶ አባልነት ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ ‹‹ እንዴት ተደርጎ!›› የሚል አቋም ይዛ የነበረችው ቱርክ፣ መለሳለስ አሳይታለች ተብሏል፡፡

ሄልሲንኪ እና ስቶኮልም በአንካራ ተቃውሞ ሳቢያ አባልነቱን ሊያጡ እንደሚችሉም ሲነገር ቆይቷል፡፡
ሃገራቱ ከሩስያ ሊቃጣብን ይችላል ያሉትን የጥቃት ስጋት መሸሸጊያ ይሆናቸው ዘንድ በማሰብ አባልነቱን ያቀረቡ ሲሆን፣ የቱርክንም ተቃውሞ ለማርገብ ብርቱ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡

ቱርክ ሃገራቱ የኩርድ ታጣቂዎችን በማስታጠቅ ለሉዓላዊነቴ ስጋት ሆነውብኝ ነበር ስትል የኖርዲክ ሃገራትን ትወነጅላለች፡፡
ስዊድንና ፊላንድ ደግሞ ውንጀላውን በይፋ ባያጣጥሉም፣ በዲፕሎማሲ ቻናሎቻቸው አንካራን ሰቅዘው በመያዝ ከአቋሟ እንድትለሳለስ አድርገዋል ተብሏል፡፡

ከሃገራቱ ባሻገር የፕሬዝደንት ሪሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ቃል አቀባይ ከዲፕሎማቶቹ ጋር የነበረውን ቆይታ ‹‹አዎንታዊ›› ሲሉም ገልፀውታል፡፡
በውይይታቸውም ሃገራቱ የጦር መሳሪያ ዝውውር ቁጥጥር እንደሚደርጉ ይጠበቃል ሲል አር ቲ ዘግቧል፡፡

በአብዱሰላም አንሳር
ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply