ስዊድን ኔቶን በይፋ መቀላቀሏን ተገለፀ።ስዊድን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅትን (NATO)ን በይፋ ተቀላቅላለች።ስዊድን በተለይ የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ቡድኑን የ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/j8wua6qs72RFXv5w6awJANb65ReW93oSMiqpjPL44FGaoZo8gtAPNcvbL1yN4lL2uMlvUHflYUatK2RHV0uX5vbenPBO1-U99rw9OdctVaY-yEQv8WlVRDNnuA4MHlLDyoE_x19fM81TyXF6HIwz5X3ab5xVTj4GqIWQeZG44s9mm8Izg2BaMzYMwAV_-QDcZ8c7Gy4eF3AdlFEwXvha2inzZwjIhv3QWMQi0ca6t1f6hd4X6u03KTPVcN9bPfiRkCE1EF2U1wEc1U0tfxAH-T7HZhmUERwgOZgf2Cy8GgZeZDmML9yLI67GfBsGuFMzFXkA4DfCvlGeGS29CVkEGA.jpg

ስዊድን ኔቶን በይፋ መቀላቀሏን ተገለፀ።

ስዊድን የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅትን (NATO)ን በይፋ ተቀላቅላለች።

ስዊድን በተለይ የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ቡድኑን የመቀላቀል ፍላጎቷ ጨምሮ እንደነበር ተነግሯል።

ሀገሪቱ ከብዙ ውጣውረድ በኋላ የኔቶ 32ኛ አባል ሀገር ሁና መቀላቀሏ ሰሞኑን ተረጋግጧል።

“የኖርድክ ሀገር ስለተቀላቀለችን ደስታ ይሰማናል” ስትል አሜሪካ የስዊድን መምጣት አሞካሽታለች።

የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሽ ሱናክም በበኩላቸዉ “ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ ነዉ” ሲሉ ገልፀዉታል።

ፊንላንድ በ2023 ከስዊድን ቀድማ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅትን መቀላቀሏ የሚታወስ ሲሆን፣ ሲዉድን 32ኛዎ የኔቶ አባል ሆኛ ተቀላቅላለች።

ኔቶ ቀጣይ ዓመታዊ ጉባኢዉን በሐምሌ ወር በዋሺንግተን ዲሲ የሚያደርግ ሲሆን የጥምረቱን 75ኛ ዓመት የሚያከብር መሆኑን የCNN ዘገባ ያመላክታል።

በአቤል ደጀኔ

የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply