ስደተኝነት የጥቂት ሀገራት ችግር ብቻ አለመኾኑን መገንዘብ እንደሚገባ ተገለጸ።

ባሕር ዳር: ሰኔ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዓለም የስደተኞች ቀን ዛሬ ሲከበር ስደተኝነት የጥቂት ሀገራት ችግር ብቻ አለመኾኑን መገንዘብ እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ በዓለም የሚገኝ የትኛውም ሀገር ስደተኝነትን የመቀበል ወይም የመፍጠር አጋጣሚ ይኖረዋል፡፡ ይህ እውነታም ስደተኞችን ሰብዓዊ በኾነ መንገድ ማክበር፣ መጠበቅ እና መንከባከብ እንደሚገባ ያስረዳል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የሃብት እጥረት እያለባቸው ድንበራቸውን ለስደተኞች ክፍት አድርገው የሚቀበሉ የአፍሪካ ሀገራትን አመሥግኗል፡፡ […]

Source: Link to the Post

Leave a Reply