‘ስፔስ ኤክስ ድራገን’ ከዓለም አቀፍ ጣቢያው ጋር ተገናኘች

https://gdb.voanews.com/61787b76-da00-4678-ab16-74723e458e01_w800_h450.jpg

ሁለት የአሜሪካ የጠፈር ሳይንቲስቶች እንዲሁም አንድ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ሌላ ሩሲያዊ ሳይንቲስት በአለም ዓቀፉ የሕዋ ጣቢያ ላይ በሰላም ማረፋቸውን የአሜሪካው የሕዋ ምርምር ተቋም (ናሳ) አስታውቋል።

ስፔስ ኤክስ ድራገን የተሰኘችው መንኩራኩር ከዓለም አቀፍ ጣቢያው ጋር ዛሬ ዓርብ መግጠሙንም ናሳ አስታውቋል።

ናሳ በለቀቀው ቪዲዮ በዓለም አቀፉ ጣቢያ የነበሩት ባልደረቦቻቸው ለአራቱ ሳይንትስቶች ሞቅ ያለ አቀባበል ሲያደርጉላቸው አሳይቷል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትሱ የ 41 ዓመቱ ሱልጣን አልነያዲ ለአገሩ ወደ ሕዋ ሲበር ሁለተኛው ሰው ሲሆን፣ ለኤምሬቷ ከአሜሪካ ምድር ላይ የመጠቀ የመጀመሪያው ሆኗል።

አዲሶቹ የሕዋ እንግዶች ለስድስት ወራት ሲቆዩ፣ 200 የሚሆኑ ሳይንሳዊ ሙከራዎችንና የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይፈትሻሉ። በዓለም አቀፉ ጣቢያ ያሉትን ሳይቲስቶች ቁጥርም ወደ 11 አሳድገዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply