የሶማሊያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምሲ አብዲ ባሬ ሃማስ የፍልስጠየማዉያንን መሬት ለማስመለስ የሚታገል ነጻ አዉጪ እንጅ አሸባሪ አይደለም ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሶማሊያ በሀገር ቤት በአልሻባብ እየተፈተነች ቢሆንም በዚህ ወቅት ግን ፍልስጤማዉያንን ልነረሳቸዉ አንችልም ነዉ ሉት፡፡
የአረቡ አለም ሀገራት እርስበእርሳቸዉ እንዲዋጉ የሚሰሩ ኃይሎች መኖራቸዉን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ ነገር ግን ሃማስ ሽብርተኛ ቡድን ነዉ የሚለዉን እንደማይቀበሉት ተናግረዋል፡፡
አለም የታለ? የሰባዊ መብት ተቆርቋሪዎችስ የት ገቡ? ሲሉም በንግግራቸዉ ጠይቀዋል፡፡
ሶማሊያ እየሩሰሌም የፍልስጤሞች ዋና ከተማ ሆና እስከሚወሰን ድረስ ወደ ኋላ እንደማትልም ገልፀዋል፡፡
አሁን ላይ ፍልስጠየማዉያኑ በጋዛ እየከፈሉት ያለዉ መስዋትነት የአል አቅሳ ነጻነት መጀመሪያን የሚመላክት ሲሉም ጠርተዉታል፡፡
በመጨረሻም ፕሬዝዳንቱ ሁላችንንም ሊያስማማን የሚችለዉ ሁለቱም ወገኖች በሰላማዊ መንገድ ሲነጋገሩ ብቻ ነዉ ማለታቸዉን ሆርን ዲፕሎማት አስነብቧል፡፡
በአባቱ መረቀ
ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም
Source: Link to the Post