ሶማሊያ ለኬንያ ዜጎች ፈቅዳው የነበረውን የጉዞ መዳረሻ ቪዛ መከልከሏን ይፋ አደረገች::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 29፣ 2013 ሶማሊያ ለኬንያ ዜጎች ፈቅዳው የነበረውን የጉዞ መዳረሻ ቪዛ መከልከሏን ይፋ አደረገች:: በሁለቱ ሀገራት መካከል በቅርቡ የጠፈጠረው የዲፕሎማሲ መሻከር ነወ ሶማሊያን ለዚህ ወሳኔ ያነሳሳት ተብሏል፡፡ የሶማሊያ ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች ባለስልጣን መስሪያቤት ከዚህ በኋላ ወደ ሶማሊያ የሚጓዙ ኬንያዊያን አስቀድመው ቪዛ ማስመታት ይጠበቅባቸዋል ብሏል፡፡

አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የዲፕሎማሲ ጉዙ የሚያደርጉ ግለሰቦች ሳይቀሩ ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በቅድሚያ ፈቃድ የማግኘት ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተፈጠረው ውዝግብ ምክንያት ኬንያ በሶማሊያ የሚገኙ ልኡኳን ወደ ናይሮቢ ጠርታለች ተብሏል ምንም እንኳ ኬንያ ነገሩን ብታስተባብልም፡፡ ጎረቤታሞቹ በባህር ድንበር አካባቢ ውዝግብ ውስጥ በመግባታቸው የተነሳ ጉዳዩ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት እንዲያልቅ በኬንያ በኩል ሀሳብ ቢቀርብም ሶማሊያ ጉዳዩን ውድቅ አድርጋዋለች፡፡

ሞቃዲሾ በኮሮናቫይረስ ምክንያት የኬንያ ተጓዦችን ወደሀገሯ እንዳይገቡ ከልክላ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ጫት መላክንም አግዳለች ነው የተባለው፡፡
ሶማሊያ ያሳለፈችው የጉዞ መዳረሻ ቪዛ ክልከላ ከዲሴምበር 13 ጀምሮ ተግባረዊ እደሚሆን የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት ተናግረዋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply