ሶማሊያ በኢትዮጵያ የሚገኙ አምባሳደሯን መጥራቷን አስታወቀች፡፡

በኢትዮጵያና በሶማሊላንድ መካከል የተደረሰዉን የመግባቢያ ስምምነት ተከተሎ ሞቃዲሾ አምባሳደሯን ከኢትዮጵያ በአስቸኳይ መጥራቷ ተሰምቷል፡፡

የሶማሊያ ካቢኔ ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን ተከትሎ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በኢትዮጵያ የሚገኙትን የአገሪቱን አምባሳደር ጠርቷል፡፡

የሶማሊያዉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ የትናንቱን ስምምነት ተቃዉመዉታል ሲል የዘገበዉ ፍራንስ 24 ነዉ፡፡

የቀድሞዉ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሙሃመድ ፋርማጆ በበኩላቸዉ ስምምነቱን ለሶማሊያ ስጋት የሚደቅን ነዉ ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ኢትዮጵያን የባሕር በር ለማግኘት የሚያስችላትን የመግባቢያ ሰነድ በተናትናዉ ዕለት መፈራረማቸው የሚታወስ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ
ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply