ሶማሊያ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቴን ታክብር ስትል በአለም አቀፍ መድረክ ላይ ቅሬታዋን ማሰማቷ ተገለጸ።

ኢትዮጵያን ጨምሮ 120 ሃገራት በሚሳተፉበት የገለልተኛ ሃገራ ንቅናቄ ላይ ሱማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር በገባችበት ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ዙሪያ ስሞታ ማቅረቧ ተሰምቷል።

አገሪቷ 19ኛ ጉባዔውን በካምፓላ እያካሄደ ላለው የገለልተኛ አገራት ንቅናቄ ላይ፣ ኢትዮጵያ የግዛት አንድነቴን ልታከበር ይገባል ስትል አቤቱታዋን ማሰማቷን ዘገባዎቹ አመልክተዋል።

የሱማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ከፍተኛ ባለስልጣን ሐምዛ አዳን፣ ድንበራችን በዓለማቀፍ ሕግ መሠረት ሊከበር ይገባዋል በማለት ለጉባዔው መናገራቸውን ዜና ምንጮቹ ጠቅሰዋል።

የገለልተኛ አገሮች ንቅናቄ ከጦርነት ለማገገም የምንጥር አገር መኾናችን ከግምት በማስገባት ድጋፉን እንዲሰጠን እንጠይቃለን ያሉት ሐምዛ አዳን፣ ሉዓላዊነታችንና የግዛት አንድነታችን እንድንጠብቅ ሊያግዘን ይገባል በማለት ጠይቀዋል።

በለዓለም አሰፋ
ጥር 08 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply