ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ለመክፈት አላቀደችም ሲሉ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ገለፁ

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ እሁድ እለት በአል አረቢያ ብሮድካስት እንደተናገሩት “ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ለመክፈት እቅድም ሆነ አላማ የለንም ሲሉ ተደምጠዋል።

ኢትዮጵያ ያልሆኑ ስራዎችን መስራት ከጀመረች ግን በዲፕሎማሲው መስክ ከየትኛውም ቦታ ድጋፍ እንፈልጋለን” ብለዋል።

በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል የተደረሰው የመግባቢያ ስምምነት የአለም አቀፍ ህግን የጣሰ እና “አክራሪዎችን የመመልመያ መሳሪያ” ነውም ሲሉ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በበኩሏ ከሶማሌላንድ ጋር የተደረገው ስምምነት የባህር በር ለሌላት ሀገር ቀይ ባህርን ተጠቃሚ ለማድረግ ያሰበ እና በአፍሪካ በህዝብ ብዛት ሁለተኛ የምትገኝ ሀገር ለቀጣናው ሰላም እና ፀጥታ ትልቅ ሚና እንድትጫወት ለማድረግ ያለመ ነው ስትል ተናግራለች።

ባሳለፍነው ሳምንት የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ አዲስ አበባ ከሶማሌላንድ ግዛት ጋር የገባችውን የመግባቢያ ስምምነት እስካልሻረች ድረስ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ግንኙነት ወደ መደበኛው ለማድረግ የሶስተኛ ወገኖችን ማንኛውንም የሽምግልና ጥረት እንደማትቀበል መግለጿ ይታወሳል።

ለአለም አሰፋ
ጥር 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply