ሶስቱ ሀገራት በሰባት ቀናት የሶስትዮሽ ድርድሩን በማካሄድ በቀጣይ አካሄዶች እና የጊዜ ሰሌዳ ስምምነት ላይ ለመድረስ መግባባታቸው ተገለጸ

ሶስቱ ሀገራት በሰባት ቀናት የሶስትዮሽ ድርድሩን በማካሄድ በቀጣይ አካሄዶች እና የጊዜ ሰሌዳ ስምምነት ላይ ለመድረስ መግባባታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በሰባት ቀናት ውስጥ የሶስትዮሽ ድርድሩን በማካሄድ በቀጣይ የድርድሩ አካሄዶች እና የጊዜ ሰሌዳ ስምምነት ላይ ለመድረስ መግባባታቸው ተገለጸ::

ሀገራቱ በሰባት ቀናት ውስጥ ድርድሩን በማካሄድ በቀጣይ የድርድሩ አካሄዶች እና የጊዜ ሰሌዳ ላይ ስምምነት መድረስ፣ ልዩነት ባሏቸው ጉዳዮች ዙሪያ ልዩነትን ለማጥበብ እና ውጤቱንም ለውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ቀጣይ ስብሰባ ለማቅረብ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል።

የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ትብብር ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት አስፈጻሚ ምክር ቤት ሊቀመንበር ቀደም ብሎ በጥቅምት 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ለሃገራቱ በጻፉት ደብዳቤ እና ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጥቅምት 17 ቀን 2013 ዓ.ም በበይነ-መረብ ስብሰባ አካሂዷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የውሃ፣ መሰኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር በጋራ ባወጡት ፕሬስ መግለጫ፤ ስብሰባው በአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ስር እየተካሄደ ያለው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የተመለከተው የሶስትዮሽ ድርድር በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ መክሯል።

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲይርል ራማፎዛ ቀደም ብሎ በጥቅምት መጀመሪያ ከኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መሪዎች ጋር በስልክ ባደረጓቸው ውይይቶች በተደረሰው መግባባት እና ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ድርድሩን ለመቀጠል ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

የመጀመሪያው የቴክኒክ ስብሰባም በሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትር ሰብሳቢነት ይከናወናል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

The post ሶስቱ ሀገራት በሰባት ቀናት የሶስትዮሽ ድርድሩን በማካሄድ በቀጣይ አካሄዶች እና የጊዜ ሰሌዳ ስምምነት ላይ ለመድረስ መግባባታቸው ተገለጸ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply