ሶስት አርቲስቶች ለብራንድ አምባሳደርነት አምስት ሚልየን ብር ክፍያ ስምምነት ፈፀሙ

ኢትዮ ኤርስ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ስር የሚገኘው ሩቢ (Ruby) ቪዛ ኮንሰልቲንግ  አርቲስት ዳንኤል ተገኝ፣ አርቲስት ሩታ መንግሥተአብ፣ አርቲስት ሊዲያና ሰለሞን   የብራንድ አምባሳደር አርጎ የሾመ ሲሆን ከዚህም  በጥቅል አምስት ሚልየን ብር ገደማ ክፍያ ስምምነት ዛሬ በሸራተን አዲስ ፈፅመዋል።

አቶ ታረቀኝ ቶሎሳ የኢትዮ ኤርስ ንግድ እና ኢንቨስትመንት ዋና ስራ አስኪያጅ በሸራተን አዲስ ሆቴል በዛሬው ዕለት በተሰጠው መግለጫ ላይ እንደተናገሩት ኢትዮ ኤርስ እኤአ በ2007 መቋቋሙን በስሩም ለህብረተሰቡ ችግር ፈቺ የሆኑ የተለያዩ ኩባንያዎችን በማቀፍ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በኢትዮ ኤርስ ንግድና ኢንቨስትመንት ስር ከሚገኙ ተቋማት ውስጥ የዛሬው መርሐግብር በቀጥታ የሚመለከተውና በአለም አቀፍ ደረጃ ወደባሕርማዶ በስራ፣ በጉብኝት፣ በቢዝነስና በኢንቨስትመንት ቪዛ ለመሄድ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንን የቪዛ ማማከር አገልግሎት የሚሰጠው “ሩቢ”ኮንሰልቲንግ በብራንድ አምባሳደርነት ሶስቱን አርቲስቶች ሾሟል።

አርቲስቶች በሥራቸው፣ በማህበረሰቡ ባላቸው ተቀባይነትና በሥነምግባራቸው መመረጣቸው ተነግሯል።

The post ሶስት አርቲስቶች ለብራንድ አምባሳደርነት አምስት ሚልየን ብር ክፍያ ስምምነት ፈፀሙ appeared first on Fidel Post.

Source: Link to the Post

Leave a Reply