ሶስት ጊዜ እንዲሻሻል የተደረገው የእነ እስክንድር ነጋ ክስ ሆንተብሎ የተከሳሾችን ጊዜን በማባከን በቀጣዩ ምርጫ እንዳይሳተፉ ለማድረግ የታቀደ ነው ብለው እንደሚያምኑ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ተና…

ሶስት ጊዜ እንዲሻሻል የተደረገው የእነ እስክንድር ነጋ ክስ ሆንተብሎ የተከሳሾችን ጊዜን በማባከን በቀጣዩ ምርጫ እንዳይሳተፉ ለማድረግ የታቀደ ነው ብለው እንደሚያምኑ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ተና…

ሶስት ጊዜ እንዲሻሻል የተደረገው የእነ እስክንድር ነጋ ክስ ሆንተብሎ የተከሳሾችን ጊዜን በማባከን በቀጣዩ ምርጫ እንዳይሳተፉ ለማድረግ የታቀደ ነው ብለው እንደሚያምኑ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓም አዲስ አበባ ሸዋ ከአማራ ሚዲያ ማዕከል ጋር ቆይታ ያደረጉት ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ዛሬ ታህሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ጉዳያቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት እየታየላቸው ላሉት ለባልደራስ አመራሮች ጥብቅና በመቆም መገኘታቸውን አስታውቀዋል። በእለቱም ለሶስተኛ ጊዜ እንዲሻሻል የተደረገውን ክስ ዳኛ አልተመለከትኩትምና መርምሬ አስተያት ለመስጠት ያመቸኝ ዘንድ አጭር ቀጠሮ ያስፈልገኛል በማለት ለፊታችን አርብ ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ጠበቃ ሄኖክ ክሱ ምንም እንኳ ሶስት ጊዜ እንደተሻሻለ ቢነገርም ከመሰረታዊ ይዘቱ ጋር ልዩነት የለውም እንዲያውም በእስር ላይ ያሉት የባልደራስ አመራሮች እነ አቶ እስክንድር ነጋ፣ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩምና አስካለ ደምሌ በቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ እንዳይሳተፉ ለማድረግ ያለመ አካሄድ ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልፀው፣ ቀጣይ ይሻሻል ላለመባሉም እርግጠኛ አይደለንም ብለዋል። ዘገዬ ፍትህ እንዳልተሰጠ ይቆጠራል እንደሚባለው ከቃሊቲ ማ/ቤት የቀረቡት አቶ እስክንድር ነጋም ቀልጣፋ የፍትህ አገልግሎት እንዲሰጣቸው በድጋሜ ጠይቀዋል። አስቴር ስዩም ከህክምና አገልግሎት፣ ከጠበቃ እና ቤተሰብ ግንኙነት ጋር በተያያዘ አቤቱታ ያቀረበች ሲሆን ችሎቱም ተገቢ ነው ያለውን ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይኸውም ላጋጠማት የጀርባ ህመም በግል በመረጠችው የጤና ተቋም መታከም የምትችልበት ሁኔታ እንዲመቻችላት ትዕዛዝ ስለመስጠቱ ከጠበቃ ሄኖክ አክሊሉና ከወ/ሮ አስቴር ባለቤት ከመ/ር በለጠ ጌትነትና የተገኘው መረጃ አመልክቷል። ከጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ጋር የተደረገውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ መከታተል ይችላሉ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply