“ሸኔም ይሁን የትኛውም አሸባሪ ቡድን በጀመርነውን መንገድ ጉዞአችንን አጠናክረን የምንቀጥል ከሆነ ይጠፋሉ“ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ

ሐሙስ ሰኔ 30 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) “የንፁሃንን ደም በከንቱ የሚያፈሱ የትኛውም ስብስብ፤ ሸኔም ይሁን ሌላ አሸባሪ ሀይል በጀመርነው መንገድ ጉዞአችንን አጠናክረን የምንቀጥል ከሆነ ይጠፋሉ” ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ አስቀድመውም በአገራችን በግፍ ሕይወታቸውን ላጡ፣ ለተገደሉ ንፁኃን ዜጎች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ለምክር ቤቱ ገልፀዋል።

ዜጎች ባልሰሩት ወንጀል፣ በማይመለከታቸው ጉዳይ፣ በአገራቸው በቄያቸው ሕይወታቸውን ለማሻሻል ደፋ ቀና ሲሉ ባልተገባ መንገድ ሕይወታቸውን የሚቀጥፉ ገዳዮች፣ አጥፊ ስብስቦች ያደረሱባቸው ጥቃት በእጅጉ የሚያሳዝነን ከመሆኑም ባሻገር ሕይወታቸውን ለመታደግ ባለመቻላችን እንደ አገር፣ እንደ መንግስት እንደ ሕዝብ ጥልቅ ሀዘን ይሰማናል ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የጥፋት ሀይሎች አላማ የላቸውም፣ ግብ የላቸውም፣ እሳቤአቸው ጥፋት ስለሆነ የእኛን ጉዞ ማደናቀፍ አይችሉም። መፈተን ይችላሉ፣ ፈትነዋልም ግን ማሸነፍ አይችሉም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በአጠቃላይ የሽብር እና የጥፋት ሃይሎች ኢትዮጵያዊያንን መግደል፣ ማጎሰቆል መግፋት ማሸበር ይችሉ እንደሆን እንጂ ከዋንኛው አላማችን ሊያስቀሩን አይችሉም ብለዋል።

ይህም ሆኖ ኢትዮጵያውስጥ የሚደረገው ግድያ አንዳንዶች እንደሚገልፁት መንግስት በቸልታ ስለሚሰራና ሃላፊነቱን ስለማይወጣ ተደርጎ መወሰድ የለበትም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ፣ መንግስት 24 ሰዓት የዜጎቹን ህይወት ለመታደግ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል በዚህም በርካታ ህይወት መታደግ ችሏል ሲሉም ገልፀዋል።

በማይመች ሁኔታ ውስጥ ሆነው ነው የጸጥታ ሃይሎቻችን ዋጋ እየከፈሉ ያሉት፤ ለእነሱ ክብር መስጠት ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የሚፈጠሩ የጸጥታ ስጋቶችን ለማረጋጋትም የጸጥታ አካላት ዉድ ህይወታቸዉን እያጡበትም ነዉ ሲሉ ተናግረዋል።

ለአብነትም በቅርቡ በወለጋ ደምቢዶሎ እና ጊምቢ ፣ ጋምቤላ፣ አሙሮ በተከታታይ በነበረ ግጭትና በተፈጸመሙ ጥቃትቶች በርካታ የጸጥታ ሀይሎች ህወታቸዉን አጥተዉበታል፤ደ ራሼ ላይም የወረዳ አመራሮችን እና የጸጥታ አካላትን ጨምሮ 80 የሚሆኑ ሰዎች ህይወት አልፏልም ብለዋል።

ሽብር የዓለም ኹሉ ፈተና ነው፤ በኢትዮጵ ውስጥ ብቻ የሚፈጸም አድርገን ማሰብ የለብንም፤ ሽብር መልኩ ብዙ ነው ሺሉም በመግለፅ፤ በዓለም ላይ እንድ አሜሪካ ጠንካራ የደህንነት ተቋመ ያለው አገር የለም፤ ነገር ግን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እንደተገደሉባትም አንስተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም፤ አሸባሪዎችን ከዘር ጋር ብቻ ማያያዝ ተገቢ አይደለም ያሉ ሲሆን፤ የአልሸባብ አብዛኛው ታጣቂ ሶማሌ ነው፤ በቡድኑ የሚገደለውም ሶማሌ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የግራጫ ጦርነት ነው፤ የግራጫ ጦርነት ሲባል አንደኛው የመረጃ ጦርነት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ የመረጃ ጦርነት ኢትዮጵያ ለማስቆም ትሞክራለች ግን ብቻዋን አትችለውም ብለዋል።

እንዲሁም ኹለተኛው ጦርነት የዲፕሎማሲ ጦርነት ሲሆን ሦስተኛው የሳይበር ጦርነት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ፤ ለተከበረው ምክርቤት የማርጋግጠው የምፈልገው ማንም አገር ከኢትዮጵያ ጋር ተዋግቶ ማሸነፍ ማፍረስ እንደማይችል ነው ብለዋ

ይሄ ሲባል ግን ጠላቶቻችን አረፈው ይተኛሉ ማለት አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ዛሬ በሰሜን ነገ በሌላ አቅጣጫ ኹሉ ይመጣሉ፤ ለዚህ ዙሪያ መለስ ጦርነት ቀድመን ስለተረዳን መከላከያን አጠናክረናል፤ ዛሬ ያለው መከላከያ ሰራዊት ትናንት የነበረው አይደለም፤ በኹሉም መልኩ እጅግ የተኛለ ነው፤ ለዛሬ ብቻ ሳይሆን ለነገ ትውልድ ጭምር የሚሆን መከላከያ ተገንብቷል፤ ይሄንን በዓይናችሁ አይታችኋል ሲሉም ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

መከላከያ ሰራዊት በዚህ የቅድመ ዝግጅት ሥራው ቢያንስ 95 በመቶ ተሳክቶለታል ሲሉም ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አስረድተዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply