‹‹ ሸኔን ህዝቡ ለምን ተሸከመው? ብሎ መጠየቅ ይገባል ›› አሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከኦሮሞ ህዝብ እና ከጸጥታ ሀይሎች ጋር በደንብ መነጋገር ይፈልጋል ብለዋል፡፡‹‹ ወታደራዊ እና ፖለቲካ…

‹‹ ሸኔን ህዝቡ ለምን ተሸከመው? ብሎ መጠየቅ ይገባል ›› አሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ከኦሮሞ ህዝብ እና ከጸጥታ ሀይሎች ጋር በደንብ መነጋገር ይፈልጋል ብለዋል፡፡

‹‹ ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ስራውን አስታርቆ መሄድ እንደሚያስፈልግ፣ እንዲሁም ችግር ካለም ማየት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ሸኔን ለማጥፋት ወታደራዊ ስራ ብቻውን የሚያመጣው ለውጥ የለም›› ሲሉም አክለዋል፡፡

ህዝቡ ለምን ተሸከመው ? ለምንድነው የሆነ አንድ ወረዳ የቀለበው ፤ የደበቀው? ምን ችግር ስላለ ነው? የሚለውን ቀርቦ መነጋገር እንደሚያስፈልግ አንስተዋል ፡፡

‹‹ አሁን ለምን በረታ ለምን ጉልበት አወጣ የሚሉ አሉ፡፡ ምክንያቱም ብዙ ደጋፊ ስላለ ነው፤ አሁን ብዙ አሰልጣኝ አለው ፤ ብዙ አስታጣቂ ፤ብዙም ገንዘብ ሰጪ›› አለው ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ‹‹ ሸኔ አላማ የለውም ፡፡ ምንም የተጻፈ ነገር የሌለው መሪ አልባ ነው›› ብለውታል፡፡

‹‹ለኦሮሞ ህዝብ እታገላለሁ የሚል አንድ ቡድን እንዴት የኦሮሞን ህዝብ ልማት ያወድማል?›› ሲሉም ይጠይቃሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

‹‹ቡድኑ አንድ ቦታ ሆኖ የሚዋጋ አይደለም ህዝብ እና ወታደር ከተባበረ ግን ችግሩ ይፈታል›› ብለዋል፡፡

ሸኔም፤ ህውሓትም ፤ ቤኒሻንጉልም ሌላውም ኃይል ግን ፍጹም ኢትዮጵያን አያሽፍም ይህ ከንቱ ፍላጎት ከንቱ ድካም ነው፡፡

ሰው ሊገድል ይችላል ፤ ግን አያሸንፍም፡፡ መግደሉን እንዲያቆም በተባበረ ክንድ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልጸው ፤ መካስስ ሳይሆን ተባበሩ እንዲህ አይነቱን ነገር ማስቆም ይቻላል ነው ያሉት።

ያይኔአበባ ሻምበል
የካቲት 15 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply