ሸዋ ፋኖ በአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ መኮይ ከተማ ያሰለጠናቸውን አባላት በድምቀት አስመረቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሸዋ ፋኖ ከ…

ሸዋ ፋኖ በአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ መኮይ ከተማ ያሰለጠናቸውን አባላት በድምቀት አስመረቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሸዋ ፋኖ ከአሁን ቀደም በተለያዩ አካባቢዎች ያሰለጠናቸውን ፋኖዎች ማስመረቁ ይታወሳል። ጥቅምት 21 ቀን 2014 ደግሞ በአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ ያሰለጠናቸውን 300 የሚሆኑ አባላቱን በከፍተኛ ድምቀት አስመርቋል። ከሁሉም አስቀድሞ በዝግጅቱ የተገኙት የሀይማኖት አባቶች በተለያዩ ጊዜያት ለአማራ ህዝብ መብት፣ ጥቅምና ፍላጎት መከበር ሲሉ ለተሰው ጀግኖች ጸሎት አስደርገዋል። በመድረኩም የሸዋ ፋኖ አስተባባሪ ፋኖ ሽመልስ ንጉሴ፣ ተስፋ እሸቴ፣ ከክብር እንግዶች ዶ/ር ወንድ ወሰን አሰፋ፣ የአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደምስ፣ የፋኖ አመራሮችና አባላት፣ የአማራ ልዩ ኃይልና የፖሊስ አባላት፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የመኮይ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል። በዝግጅቱም የእንኳን ደስአላችሁ መልዕክት የተላለፈ ሲሆን አርቲስት መብሬ መንግስቴ መድረኩን “ዋ በለው መሬው” እና “መውዜር አማረኝ” በማቅረብ አድምቆት ውሏል፤ የፋኖ አባላትም ልዩ ልዩ ወታደራዊ ትርኢት እና የስነ ጹሁፍ ስራዎችን አቅርበዋል። በእለቱም ለፋኖ የገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብር ተከናውኗል፤ በመድረኩም ከ192 ሽህ ብር በላይ በተሳታፊዎች ድጋፍ ሲደረግ 87 ሽህ ብር ደግሞ ቃል ተገብቷል። የእውቅና እና የምስጋና ሽልማትም ተከናውኗል፤ በዚህም የሸዋ ፋኖ አስተባባሪዎች፣ የአንጾኪያ ገምዛ የፋኖ አሰልጣኞች፣ የወረዳው አስተዳዳሪ እና ሌሎችም ተሸልመዋል። በዝግጅቱ የተገኙ የክብር እንግዶች፣ የሸዋ ፋኖ የበላይ አስተባባሪዎች፣ ሰልጣኝ የፋኖ አባላት እና ሌሎችም ህዝቡም ሆነ መስተዳድሩ ከፋኖ ጎን በመሰለፍ ያደረጉትን ሁለንተናዊ ድጋፍ የበለጠ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አድርገዋል። በመጨረሻም የአንጾኪያ ገምዛ አስተዳዳሪ አቶ ደምስ የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ የገጠመውን ፈተና ያለምንም ልዩነት በተደራጀ መልኩ ታግሎ ለማሸነፍ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply