ሸዋ_ደራ ጸሀፊ ፦ ሽመልስ_ንጉሴ_የቀድሞ_የደራ_አማራ_ማንነት_አስመላሽ_ኮሚቴ_ም/ሰብሳቢ         ደራ ወረዳ  እስከ 1996 ዓ.ም ድረስ ተጠሪነቱ  በአማራ ክልል ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዞን…

ሸዋ_ደራ ጸሀፊ ፦ ሽመልስ_ንጉሴ_የቀድሞ_የደራ_አማራ_ማንነት_አስመላሽ_ኮሚቴ_ም/ሰብሳቢ ደራ ወረዳ እስከ 1996 ዓ.ም ድረስ ተጠሪነቱ በአማራ ክልል ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዞን…

ሸዋ_ደራ ጸሀፊ ፦ ሽመልስ_ንጉሴ_የቀድሞ_የደራ_አማራ_ማንነት_አስመላሽ_ኮሚቴ_ም/ሰብሳቢ ደራ ወረዳ እስከ 1996 ዓ.ም ድረስ ተጠሪነቱ በአማራ ክልል ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዞን በመርሃቤቴ አውራጃ ነበር። ነገር ግን ደራ ከ 1996 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ኦሮሚያ ክልል የተካለለ እና ከዚህ ግዜ ጀምሮ የማንነት ጥያቄ ከደራ ነዋሪዋችም ከ ከሞላው አማራ በየወቅቱ ሲጠየቅ የነበረ ጥያቄ ነው ።… ይሁንና ይህንን የማንነት ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ ለምን ጠየቃችሁ በሚል ተልካሻ ምክንያት ብዙዋች ተገለዋል ብዙዎች ሃገር ለቀው ጠፍተዋል ። ሞተው ሬሳቸው ከተገኙት ውጪም ሬሳቸው ያልተገኘ ብዙሃን ወገኖቻችን አሉ። ከሰቆቃው ገፈት ቀማሾች መሃል😡 በቁጥር ለመግለጽ ያህል 1) 1ሺ በላይ ሰው ሞቷል 2) በማንነታቸው ብቻ ጫና ሲፈጠርባቸው ሃገር ለቀው ወደ ጅቡቲ የተሰደዱ ቁጥራቸው 25ሺህ የሚደርስ ሆኖል። 3) አካባቢው ላይ በጫና ምክንያት መስራት እና መኖር ሳይችሉ ሲቀሩ ወደ አዲስ አበባ÷ሰላሌ ፊቼ÷ሱሉልታ እና ሌሎችም ቦታወች ተፈናቅለው በተለይ አዲስ አበባ ቀጨኔ ሽሮ ሜዳ በበረንዳ ላይ ያሉ ቁጥራቸው ወደ 10ሺህ የሚደርስ አማራወች ዋጋ እየከፈሉ ይገኛል ይህ መሰዋእትነት የተከፈለበት የደራ ጥያቄ በደሉና ሰቆቃው የበዛ ሲሆን ላለመሞት እና ጥያቄው ቀለል ብሎ በፍጥነት መልስ እንዴገኝ ከነበር ጉጉት ጥያቄው በልዩ ዞን እንተዳደር ጥያቄነት በቆራጥ ወንድሞቻችን ተጀምሮ እኛ ጋር ደርሷል እኛም ጥያቄው ስህተት ቢኖርበትም ተቀብለን በትግል ላይ እንገኛለን ። ነገር ግን መስተካከል እና ትክክለኛው ከዚህ በሆላ ቅደም ተከተሉን ጠብቆ የደራ ጥያቄ #ወደ_ነበርንበት ክልል የመመለስ እንቅስቃሴው እንደገና በርትቶና ተጠናክሮ መላው የሸዋን ህዝብ ባማከለ መልኩ እንዲሁም መላው አማራን ባማከለ መልኩ የእርስታችንን ጥያቄ የምንቀጥል ይሆናል። ደራ አማራ ነው ኦሮሞ ነኝ የምትሉ አንዳንድ አካላትም ኦሮሟይዝድ ስለተደረክ እንጂ ኦሮሞ ሆነህ ያለመሆኑን ተረድታችሁ አማራው እንዳለ ሆኖ ማንኛውም የደራ ህዝብ በሙሉ ተሳትፎ ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን። ሌላው ትዝ የሚለኝ ጎደጨፌ ኦሮሞም አማራም ያለበት ሰፈር ነው ነገር ግን ህዝባዊ ኮንፍረንስ ባደረግንበት ሰአት ሁሉም ሰው ወደ መርሃቤቴ አውራጃ ወደ ሸዋ ግዛት አንዲመለስ ነበር ጥያቄው። በሌላ በኩል በዋናነት የደራ ጥያቄ የመላው ሸዋ ጥያቄ እንዲሁም የመላው አማራ ጥያቄ ነው። ሁሉም የሸዋ ህዝብ ሁሉም የአማራ ህዝብ ትኩረት ሰቶ ሊሰራበት ይገባል። ተዳከመ የተባለውን ኮሚቴ አበረታተን እና በደንብ ተጠናክረን ወደፊት አንድ እርምጃ የምንራመድ እንደሚሆን እና ስኬታማ እንደምናደርገው አልጠራጠርም ። የደራ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ብሎ ልዩ ዞን የለም። ደራ የአማራው የሸዋ ግዛት በመርሃቤቴ አውራጃ የሚተዳደር ነበር ወደነበረበትም ሙሉ በሙሉ ይመለሳል። ጥያቄያችንም ሸዋ መርሃቤቴ አውራጃ ነበርን ወደዛም ወደነበርንበት እንመለሳለን ሆና ይቀጥላል። በቀጣይ ማለትም ታህሳስ 18/04/2013 ዓ,ም በምናደርገው ስብሰባ የኮሚቴ ማስተካከያና ተጠናክሮ እንዲጓዝ በሆነ ማግስት በማንኛውም የሸዋ ጠቅላይ ግዛት በየወረዳው ኮሚቴ የምናዋቅር እና ተጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል መላው የሸዋ ህዝብ እንዲሁም ሙሉ የአማራ ህዝብ በሚያስፈልገው ሁሉ ከጎናችን እንዲሆን በድጋሚ ጥሪ እናቀርባለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply