ሺ ዢንፒንግ እና ቭላድሚር ፑቲን የጂ-20 ስብሰባን እንደሚሳተፉ መረጋገጡ ተዘግቧል፡፡የኢንዶኔዢያዉ ፕሬዝዳንት ጆኮ ዊዶዶ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በህዳር ወር በባሊ በሚካሄደዉ የጂ-20 ስብሰ…

ሺ ዢንፒንግ እና ቭላድሚር ፑቲን የጂ-20 ስብሰባን እንደሚሳተፉ መረጋገጡ ተዘግቧል፡፡

የኢንዶኔዢያዉ ፕሬዝዳንት ጆኮ ዊዶዶ የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በህዳር ወር በባሊ በሚካሄደዉ የጂ-20 ስብሰባ እንደሚሳተፉ ማረጋገጣቸዉን ገልጸዋል፡፡

‹‹ሺ ዢንፒንግ ይመጣሉ፣ ፕሬዝዳንት ፑቲንም እንደሚመጡ አሳዉቀዉኛል›› ሲሉ መሪዎቹ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚገኙ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል፡፡

በህዳር ወር በኢንዶኒዢያዋ ባሊ የሚካሄደዉ ይህ ስብሰባ የሩሲያዉ ፑቲን፣የቻይናዉ ሺ እና የአሜሪካዉ ጆ ባይደን፣ ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች እና ከአዉሮፓ ህብረትም እንዲሁም ከ ጂ-20 አባል ሀገራት ብዙ ማዕቀቦች ከተጣሉባት በኋላ በአካል የሚገናኙበት የመጀመሪያዉ ስብሰባ መሆኑ ነዉ የተዘገበዉ፡፡

ክሬምሊን ባወጣዉ መግለጫ ፑቲን እና ዊዶዶ ስለ ስብሰባዉ ዝግጅት በስልክ በስፋት መነጋገራቸዉን ገልጾ ስለ ፑቲን በስብሰባዉ ላይ መገኘት ግን ምንም ያለዉ ጉዳይ የለም፡፡
ለረጅም ጊዜ የኢንዶኔዢያዉ ፕሬዝዳንት አማካሪ የነበሩት ግለሰብ ፑቲን በስብሰባዉ ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል፡፡

ስብሰባዉ እየተዘጋጀ ባለበት በዚህ ወቅት ኢንዶኔዢያ ሩሲያን ወደ ስብሰባዉ በመጋበዟ ከምዕራቡ ዓለም ብዙ ትችት እያስተናገደች ትገኛለች፡፡
ባለፈዉ ሰኔ ወር ሁለቱን ሀገራት ለማሸማገል በማሰብ ወደ ሞስኮ እና ኬቭ የተጓዙት የኢንዶኔዢያዉ ፕሬዝዳንት ዊዶዶ ሁለቱ ሀገራት ኢንዶኔዢያን ‹‹የሰላም ድልድይ›› አድርገዉ መቀበላቸዉን ገልጸዋል፡፡

ዊዶዶ ከፑቲን ዉጭ የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜለንስኪንም ለስብሰባዉ መጋበዛቸዉን የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ.ም

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply